እዳ ያልከፈሉ እየተከሰሱ ነው‼️
በቴሌብር ዲጂታል ብድር ውዝፍ ዕዳ ላይ ህጋዊ እርምጃ እና ክስ መጀመሩ ተገለጸ‼️
ዳሸን ባንክ እና ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌብር መተግበሪያ አማካኝነት የወሰዱትን የዲጂታል ፋይናንሲንግ ብድር በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ያልከፈሉ ተበዳሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውን እና በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ክስ እየመሰረቱ እንደሚገኙ አስታወቁ።
ባንኩ ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው፣ ተበዳሪዎች ያለባቸውን ውዝፍ ዕዳ እንዲከፍሉ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም የተደረገውን የቅጣት ክፍያ ምሕረት ተጠቅመው ዕዳቸውን ያልከፈሉ ወገኖች ላይ የህግ አካሄድ መጀመሩን ገልጿል።
በመግለጫው መሠረት፣ አስቀድሞ ለቀረበላቸው ጥሪ ምላሽ ያልሰጡ ተበዳሪዎች ላይ በፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶ ከዋናው ዕዳ በተጨማሪ ባንኩ ለክስ ያወጣቸውን ልዩ ልዩ ወጪዎች እንዲሸፍኑ ውሳኔ እየተሰጠ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።
ዳሸን ባንክ አክሲዮን ማህበር የህዝብ ገንዘብ ለማስመለስ የጀመረውን ህጋዊ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመጠቆም፣ እስካሁን የክስ መጥሪያ ያልደረሳቸው ተበዳሪዎች ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ከመሄዱ በፊት እና ተጨማሪ አላስፈላጊ እንግልት እንዲሁም ወጪ ሳይደርስባቸው ያለባቸውን ዕዳ በአስቸኳይ እንዲከፍሉ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።
@Seledadotio

No comments yet.