የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሚወቀስበትን የቪዛ ችግር በስኬት አጠናቋል

- Advertisement -
Sidebar AD

🔴

🔴 ለስኬቱ ትልቁን ድርሻ የሚወስዱት የፅ/ቤት ኃላፊው አመንሲሳ ከበደ(ዶ/ር) አድናቆት እየቀረበላቸው ነው

🔴ከሰባቱ ኦፌሺያልስ የአምስቱም ቪዛ ማግኘታቸው ተረጋግጧል

#Ethiopia | የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከቪዛ ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ወቀሳ ሲቀርብበት ነበር፤እንደ ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያልም ተደጋጋሚ ዘገባ በመስራት ድርጊቱንና የፌዴሬሽኑን በተለይ ፅ/ቤቱ አሠራሩን እንዲያሻሽል የትችት ናዳ ስታወርድም ነበር፤

አሁን ደግሞ ፌዴሬሽኑ በተለይ የፅ/ቤቱ ኃላፊው አመንሲሳ ከበደ(ዶ/ር) የሚያስመሠግን ስራ በመስራታቸው በአደባባይ ልናመሠግናቸው ስኬታማ ስራቸውና የጋዜጠኝነት ሙያችን ግድ ይለናል።

ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከታማኝ ምንጮቻችን ባገኘነው መረጃ መሠረት
እ.ኤ.አ ከሐምሌ 29 እስከ ነሐሴ 3/2018 ዓ.ም በአሜሪካ ዩጂን ኦሪገን ለሚካሄደው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ለመሳተፍ የተመረጡና በዝግጅት ላይ የሚገኙ አትሌቶችና አሠልጣኞች ለጉዞ የሚያስፈልጋቸውን ቪዛ ሙሉ በሙሉ ከአሜሪካ ኤምባሲ ማግኘታቸውን አረጋግጠውልናል።

አትሌቶቹና አሠልጣኞቹ ቪዛ እንዲያገኙ በማድረጉ በኩል እንደ ፌዴሬሽን ጥረት ቢደረግም የፅ/ቤት ኃላፊው አመንሲሳ ከበደ(ዶ/ር)ለስኬቱ ሚናቸው ከፍተኛ እንደነበር እነዚሁ የመረጃ ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀውልናል።

እነዚሁ የመረጃ ምንጮቻችን ጨምረው እንደገለፁልን ፌዴሬሽኑ በተለይ ጉዳዩን በዋናነት የሚከታተሉት የፅ/ቤት ኃላፊው አመንሲሳ ከበደ(ዶ/ር) ባለፈው ከተፈጠረው ክፍተት ትምህርት በመውሰድና በቀጥታ ከሚመለከተው አካል ጋር ግንኙነት በመፍጠር የአትሌቶች፣የአሠልጣኞች፣የፌዴሬሽኑና የስፖርት ቤተሠቡ ስጋትና ራስ ምታት የሆነውን የቪዛ ችግር በማስወገድ ሙሉ የልዑካን ቡድኑ ነገ ከተቀጠሩት 7 ኦፊሺያልስ ውጪ ቪዛ አግኝተው ለጉዞ ዝግጁ መሆናቸውን በማረገጋገጥ በርካቶች ከወዲሁ የፅ/ቤት ኃላፊውን ለማመስገን ተገደዋል።

አትሌትቹና የአሠልጣኞች መቶ በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን አብረው ከሚጓዙት ሰባቱ ኦፊሺያሎች የአምስቱ የቪዛ ጉዳይም(Issued)መሆኑና የተጠናቀቀ ሲሆን ማብራሪያ የተጠየቀባቸው የቀሪዎቹ ሁለትና ሶስት የሚሆኑት ኦፊሺያሎችም በነገው ዕለት ተጠናቆ የልዑካን ቡድኑ እንደ ባለፈው በቪዛ ችግር ተንጠባጥቦ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ተሟልተው ወደ አሜሪካ ዩጂን ኦሪገን እንደሚጓዙ እነዚሁ ምጮቻችን አረጋግጠውልናል።

ከባለፈው ተሞክሮ የወሠደው ፌዴሬሽኑ በተለይ የፅ/ቤት ኃላፊው አመንሲሳ ከበደ(ዶ/ር)በውጭ ጉዳይ፣በውድድሩ አዘጋጆች(LOC) እና በወርልድ አትሌቲክስ ላይ ብቻ የተንጠለጠለ አሠራርን ብቻ ከመከተል በመውጣት በዋናነት ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ጋር በቀጥታ ግንኙነት በመፍጠር በመጀመሪያ በቪዛ አጠያየቅና ፎርም አሞላል ዙሪያ የOnline ሰልጠና ከተወሠደ በኋላ ይሄንኑ ስልጠና ለአትሌቶቹና ለአሠልጣኞቹ በመስጠት በመቀጠልም ስለ እያንዳንዱ አትሌት 14 ገፅ አጭር ፕሮፋይል በፅ/ቤት ኃላፊው ተዘጋጅቶ በመላክና በቂ ግንዛቤ እኔዲኖር በማድረግ ከቪዛ ጋር በተያያዘ የነበረውን መጥፎ ታሪክ የቀየረ ስራ እኚሁ የፅ/ቤት ኃላፊ መስራታቸውና ለቪዛው መሳካት ትልቁን ሚና መጫወታቸውን የፌዴሬሽኑ ምንጮቻችን አሳውቀውናል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሚወቀስበትን የቪዛ ችግር መቶ በመቶ በስኬት በማጠናቀቁ ብዙዎችን ያስደሠተ ሲሆን ለስኬቱም የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱት የፅ/ቤት ኃላፊው አመንሲሳ ከበደ(ዶ/ር) የቪዛ አጠያየቁን በመቀየርና በማዘመን ለስኬቱ አይነተኛ ሚና በመጫወታቸውና በቪዛ ጉዳይ ስሙ የጠለሸውንና ከህገ-ወጥ ዝውውር ጋር በተያያዘ አመኔታ አጥቶ የቆየውን የፌዴሬሽኑን ስምና ክብር የመለሠ ስራ በመስራታቸው ከየአቅጣጫው የአድናቆት ናዳ እየወረደባቸው ነው።

ለወቀሳ ብቻ ሳይሆን ጥሩ ስራ ሲሰራም ለማመስገን የማትሠስተው ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል በዚህ ስኬታማ ስራ ላይ የተሳተፉትን አካላት በቀጣይ አነጋግረን ለመምጣት ጥረት የምናደርግ ይሆናል።

✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: