የፊፋ አዲሱ እቅድና የገንዘብ ማታለያው

- Advertisement -
Sidebar AD

*የአለም ዋንጫው የኢንፋንቲኖ የግል ንብረት አይደለም፦ FA

*የእግር ኳስን ነፍስ እና ማህበራዊ እሴት ለሽያጭ አቅርቧል፦ዩ.ኤ.ፋ

#Ethiopia | የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት ጃኒ ኢንፋንቲኖ የዓለም ዋንጫ የንግድና የብሮድካስት መብቶች ዙርያ አደገኛ የተባለውን እቅድ አቅርበዋል።

ይህ ፕሬዝዳንቱ ያቀረቡት እቅድ በዓለም እግር ኳስ አስተዳዳሪዎች እና አህጉራዊ ኮንፌዴሬሽኖች ዘንድ ብርቱ ተቃውሞ እና ውዝግብ አስነስቷል።

በቀረበው እቅድ መሠረት ፊፋ Fifa forward Enterprise (FFE)
የተሰኘ 20 ቢሊዮን ዶላር ግምት ያለው ንዑስ ኩባንያ በመመስረት የዓለም ዋንጫውን የንግድ የስፖንሰርሺፕ፣ የቲኬት እና የብሮድካስት መብቶች ለዚሁ ኩባንያ ይሰጣል።

ፊፋ የዚህን ኩባንያ እስከ 20 በመቶ ድርሻ (እስከ 4.2 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ) ለውጭ የግል ባለሀብቶች ለመሸጥ አቅዷል።

ፕሬዝዳንት ጃኒ ኢንፋንቲኖ ለ211ቱ አባል ሀገራት እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች በላኩት ደብዳቤ ይህንን እቅድ እስከ መስከረም 9 (September 19) ድረስ እንዲደግፉ የጊዜ ገደብ አስቀምጠዋል።

እቅዱን ለሚደግፉ አባል ሀገራት ለታችኛው እግር ኳስና መሠረተ ልማት ልማት የሚውል እስከ 20 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ የአንድ ጊዜ ክፍያ እንደሚሰጥ ቃል ገብተዋል።

የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ፊፋ የእግር ኳስን ነፍስ እና ማህበራዊ እሴት ለሽያጭ አቅርቧል ሲል በጽኑ ኮንኗል።

ዩኤፋ (UEFA) ይህ ድርጊት ሊታለፍ የማይገባውን መስመር ያለፈ መሆኑን በመግለጽ የአውሮፓ ሀገራት ከአባልነት እስከመውጣት የሚደርስ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል።

እንደዚሁም የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር በበኩሉ የዓለም ዋንጫ የኢንፋንቲኖ ወይም የፊፋ የግል ሀብት አይደለም ሊሸጥም አይገባም ሲል ተቃውሞውን አሰምቷል።

ጃኒ ኢንፋንቲኖ የቀረበው እቅድ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ደካማ የገንዘብ አቅም ያላቸውን አባል ሀገራት ለመደገፍና የእግር ኳስ ሀብትን ፍትሐዊ በሆነ መልኩ ለማሰራጨት የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#FIFA #UEFA #Concacaf
#FIFAForwardEnterprise


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: