የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የጥንቃቄ ማሳሰቢያ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በሐዋሳ ከተማና በአካባቢዋ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ፣ በረዶ እና ኃይለኛ ንፋስ እየተከሰተ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ባለስልጣንም በቀጣዮቹ ቀናት ዝናቡ የበለጠ ሊጠናከር እንደሚችል አስጠንቅቋል።

በዛሬው ዕለት የወረደው ከባድ ዝናብ፣ በረዶ እና ኃይለኛ ንፋስ በአንዳንድ አካባቢዎች ዛፎችንና የኤሌክትሪክ ምሰሶዎችን በመጣሉ በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል። በመሠረተ ልማት ላይ በደረሰው ጉዳትም በአንዳንድ የከተማው ክፍሎች የመብራት አገልግሎት ተቋርጧል።

የከተማ አስተዳደሩ ለተጎዱ ዜጎች ያለውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ፣ ተጎጂዎችን ወደ ሕክምና ማድረስና የደረሰውን ጉዳት ለመለየት እና ድጋፍ ለማድረግ አስፈላጊ ሥራዎች መጀመራቸውን ገልጿል።

አስተዳደሩ በቀጣዮቹ ቀናት ኃይለኛ ንፋስ የታጀበ ዝናብና የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ስለሚችል ህብረተሰቡ ከዛፎች፣ ከያረጁ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች እና ከአጥሮች በመራቅ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።

በተጨማሪም ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን በመለየት የቅድመ መከላከል ሥራዎች እየተጠናከሩ መሆናቸውንና የከፋ አደጋ እንዳይደርስ አስፈላጊ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን ገልጿል።

የሐዋሳ ከተማ ኮሙኒኬሽን






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1