በመንግሥት በተገነቡ መንገዶች ላይ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ግብር ሊከፍሉ ነዉ
የምጣኔ ሀብት ባለሙያ የሆኑት አቶ ዋሲሁን በላይ ይህ ግብር በተሽከርካሪ ባለቤቶች ላይ የሚጣል ሲሆን፥ተሽከርካሪዎቹ በመንግስት በተገነቡ መንገዶች ላይ ስለሚንቀሳቀሱ በየዓመቱ የሚከፈል ይሆናል ብለዋል።
ይህም ከመደበኛው የተሽከርካሪ ዓመታዊ ምርመራ ወይም ቦሎ ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችል ግዴታ ነው።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያዉ እንደገለፁት፥ግብር አጣጣሉም እንደ ተሽከርካሪዎቹ ዓይነትና እንደሚያመነጩት ጭስ (ካርቦን) ሊለያይ እንደሚችል ተናግረዋል።
ይህ ማለት ብዙ ጭስ የሚለቁ አሮጌ ተሽከርካሪዎች ከፍተኛ ግብር እንዲከፍሉ አዳዲሶች ደግሞ ዝቅተኛ እንዲከፍሉ ሊደረግ ይችላል ተብሏል።
ይህ አሰራር በሌሎች አገራት ለምሳሌ በኬንያ፣ በሩዋንዳና በአውሮፓ አገራት የተለመደ ሲሆን፥መንግስት ለመንገድ ጥገና የሚውል ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝ ያስችለዋል።
ግብሩ በከተሞችና በክልሎች የሚሰበሰብ በመሆኑ የአካባቢ መስተዳድሮች የራሳቸውን የልማት በጀት እንዲያሳድጉ ትልቅ ዕድል ስለሚፈጥርላቸው በፌዴራል መንግስት ላይ ያለውን የገንዘብ ጫና ይቀንሳል።
ይህ የታክስ ፕሮፖዛል በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ለማቅረብ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡
አቶ ዋሲሁን አክለዉም ዝርዝር ደንቦችና መመሪያዎች ወጥተውለት ወደ ተግባር እንደሚገባና የኢኮኖሚው የገቢ ምንጭ እንደሚሆን እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
ከዚህ ግብር የሚገኘው ገቢ ከአጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት 0.2 በመቶ ድርሻ ይኖረዋል ተብሎ ይገመታል።
@Seledadotio

No comments yet.