ዙከርበርግ አሜሪካን አስጠነቀቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የሜታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማርክ ዙከርበርግ የአሜሪካ መንግሥትን አስጠንቅቋል።

የሀላፊው ማስጠንቀቂያ የመጣው አሜሪካ የሱፐር ኤአይ ውድድር የበላይነትን በብቸኝነት ለመቆጣጠር በሚል የቻይናን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሞዴሎችን ለማገድ እንቅስቃሴ እያደረገች መሆኗን ተከትሎ ነው።

ዙከርበርግ ከፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ እንደገለፀው የቻይናን AI ሞዴሎች ማገደ አሜሪካ በቴክኖሎጂው ዘርፍ እንድትመራ አይረዳትም ይልቁንም በዘርፉ ያለውን ነፃ የገበያ ውድድር ያጠፋዋል ብሏል።

አሜሪካ ውስጥ ያሉ የኤአይ ላቦራቶሪዎች እና ኩባንያዎች መንግሥት ጥብቅ ህጎችንና እገዳዎችን እንዲያወጣ በመገፋፋት ላይ ይገኛሉም ብሏል።

እነዚህ ተቋማት ይህንን የሚያደርጉት የገበያ የበላይነትን ብቻቸውን ለመያዝ እና ነጻ የገበያ ውድድርን ብቻቸውን ለማፈን አስበው ነው ሲል ዙከርበርግ የተናገረው።

እናም የቻይናን የላቁ ኤአይ ቴክኖሎጂዎች ማገድ መፍትሔ አለመሆኑንም ገልጿል።

ዙከርበርግ አክሎም አሜሪካውያን ኩባንያዎች የራሳቸውን ማነቆዎች በመለየትና የቴክኖሎጂ አቅማቸውን በማሳደግ በውድድር አሸንፈው ገበያውን መቆጣጠር እንዳለባቸው ተናግረዋል።

የሜታ ሀላፊ ይህንን የተናገረው
የቻይና ሞዴሎች ከአሜሪካ አቻዎቻቸው ጋር ያላቸውን የቴክኖሎጂ ልዩነት በፍጥነት እያጠበቡ መምጣታቸው በዋሽንግተን ባለሥልጣናት ዘንድ ሥጋት መፍጠሩን ተከትሎ ነው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Meta #Zuckerberg
#USA #China
#AIcompetition


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2