#Ethiopia | መንግስታት ቃላቸውን መጠበቅ ባለመቻላቸው ከ118 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በግፍ እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል ስትል ናዲያ የተናገረችው።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ በመላው አለም ከ118 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ከመኖርያ ቀያቸው ተፈናቅለው ይገኛሉ ብሏል።
ከዚህ ቁጥር ውስጥ ወደ 68 ሚሊዮን የሚጠጉት በራሳቸው ሀገር ውስጥ የተፈናቀሉ ናቸው።
ከ41.6 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ ሀገራቸውን ጥለው ወደ ሌላ ሀገር የተሰደዱ ናቸው።
የተቀሩት ከ9 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ ጥገኝነት ጥያቂዎች ናቸው።
ከ75 ዓመታት በፊት በፈረንጆቹ በ1951 የተፈረመው ዓለም አቀፉ የስደተኞች ስምምነት በዛሬው እለት እየተከበረ ይገኛል።
በዚሁ ወቅት የኖቤል የሰላም ተሸላሚዋ ናዲያ ሙራድ ለተፈናቃዮች የተገባው ቃል በተግባር እንዲገለፅ ጥሪ አቅርባለች።
በግዳጅ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች በሙሉ ሙሉ ደህንነት እና ከለላ ማግኘት እንዲችሉ አሁንም ያልተቋረጠ እና የተቀናጀ እርምጃ እንደሚያስፈልግ አሳስባለች።
መንግስታት ከ75 አመታት በፊት የገቡትን ቃል ከተራ ቃል አልፈው ወደ ተግባራዊ እርምጃ ሊለውጡት ይገባል ብላለች።
በ1951 የወጣው የስደተኞች ስምምነት ተፈናቃዮች ወይም ስደተኞች ሕይወታቸው ወይም ነጻነታቸው አደጋ ላይ ወደሚወድቅበት ሀገር በግዳጅ እንዳይመለሱ ዋስትና ይሰጣል።
እንደዚሁም ስደተኞች የመንቀሳቀስ መብታቸው የመስራት፣ የትምህርት እና የሕክምና አገልግሎቶችን የማግኘት መብት እንዲኖራቸውም ይደነግጋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#RefugeeConvention
#NobelLaureate
#Nadiamurad
Source: GetuTemesgen








No comments yet.