#Ethiopia | የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ 540 የሚሆኑ የሂሳብ ባለሙያዎች የብቃት ማረጋገጫ ፈተና አስጀምረዋል።
የተመሰከረላቸው ሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት በመካከለኛ ደረጃ አካውንቲንግ ቴክኒሻንነት ያሰለጠናቸውን 540 የሚጠጉ የሂሳብ ባለሙያዎች ፈተና እየወሰዱ ናቸው።
የማረጋገጫ ፈተናውን ያስጀመሩት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እንደተናገሩት የሀገሪቱን የፋይናንስ ስርአት በብቃት ለመምራት ብቃት ያለው የሰው ሀይል ያስፈልጋል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ ስር በህግ የተቋቋመው የተመሰከረላቸው ሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት ነው ፈተናውን እየሰጠ የሚገኘው።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ አጎናፈር ከሰኞ ሐምሌ 20 ጀምሮ እስከ ነገ ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በሀገሪቱ በሚገኙ 5 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተናው እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል።
በአዲስ አበባ፣ ባህርዳር፣ ጅማ፣ ሀዋሳ እና ሀሮማያ ዩኒቨርስቲዎች እየተሰጠ የሚገኘው ፈተና በ9 ሞጁሎች ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።
የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የኢንስቲትዩቱ መቋቋም በሂሳብ ሙያ ዘርፍ ብቁ ሙያተኞችን ለማፍራት እንደሚረዳም ጠቁመዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ሰርተፍኬት አግኝተው ብቁ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ብቁ የሂሳብ ባለሙያዎች ቁጥር አነስተኛ እንደሆነ ሲገለጽ ይሄንን ለመፍታት በአዋጅ ቁጥር 1372/2017 መቋቋሙ ይታወሳል።
የተመሰከረላቸው ሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት በሂሳብ ቴክኒሻን የብቃት ማረጋገጫ ስልጠና እንዲሰጡ 8 የመንግስት ዩኒቨርስቲዎችን ጨምሮ ለ11 የትምህርት ተቋማት ፈቃድ መስጠቱ ይታወሳል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#AABE #ATQ #ETICPA



Source: GetuTemesgen









No comments yet.