በሀዋሳ ከተማ በረዶ ቀላቅሎ በጣለ ከባድ ዝናብ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ
👉አደጋው በ1ሰው ላይ ከባድ እና በ8 ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት ኡድርሷል
በሀዋሳ ከተማ ትናንት ምሽት በተከሰተው ያልተለመደ ኃይለኛ ንፋስ እና በረዶ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ ምክንያት የአንድ ሰው ህይወቱ ማለፉን የከተማዋ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል።በአደጋው አንድ ሰው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ሲደርስ በ8 ሰዎች ደግሞ ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል።
የሀዋሳ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የመምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ቶርባ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በአደጋው በርካታ ቤቶች ጣሪያዎች በኃይለኛው ንፋስ ተነስተው በመውደቃቸው በሰዎችና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።በተጨማሪም የኮንክሪት የኤሌክትሪክና የቴሌ ፖሎች በመውደቃቸው በከተማዋ በባህል አዳራሽ ምሥራቅ እና መሀል ክፍለ ከተማዎች አካባቢ የኃይል መቋረጥ መከሰቱን ገልጸዋል።
በአደጋው ሁለት መኪኖችና አንድ ባጃጅ ላይ የዛፍ ቅርንጫፎች በመውደቃቸው የመስታወት መሰበር ጉዳት ቢደርስም ከባድ ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ተጠቁሟል። በባጃጁ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ከአደጋው በፊት ወጥተው በመጠለላቸው ከጉዳት መትረፋቸው ተገልጿል።በከተማዋ የተሰሩት የኮሪደር ልማት ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ ለአቶ ወንድሙ ብስራት ሬዲዮ ጥያቄ ያነሳ ሲሆን አዳዲስ የተሰሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች እና ቦዮች ወይም ካናሎች ጎርፍ በቀላሉ እንዲፈስ ስለረዱ ከጎርፍ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ ቀናንሰውታል በኮሪደር ልማቱ ላይ የደረሰ የጎርፍ ጉዳት የለም ሲሉ ተናግረዋል።
የከተማ አስተዳደሩና የተለያዩ አካላት በማድረግ ባሉት የመስክ ምልከታ መሠረት አስቸኳይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ሥራዎች እየተጀመሩ መሆኑ ተገልጿል።አደጋው ለ8 ደቂቃ ያህል አጭር ጊዜ ቢቆይም የንፋሱና የበረዶው መጠን ከፍተኛ እንደነበር ተጠቁሟል። ህብረተሰቡም የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃዎችን በመከታተል ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.