ወደ ስዊድን ያቀኑ 20 የእግርኳስ ቡድን አባላት መጥፋታቸው ተሰማ ወደ ስዊድን ያቀኑ ዕድሜያቸው ከ 14 እስከ 17 የሚገመት 2…

- Advertisement -
Sidebar AD
ወደ ስዊድን ያቀኑ 20 የእግርኳስ ቡድን አባላት መጥፋታቸው ተሰማ
ወደ ስዊድን ያቀኑ ዕድሜያቸው ከ 14 እስከ 17 የሚገመት 20 ታዳጊ የእግርኳስ ተጫዋቾች ከ መሪያቸው ጋር መጥፋታቸውን ስዊድን ሄራልድ ዘግቧል።
“ጎቲያካፕ” ለተሰኘ የእግር ኳስ ውድድር  ከኢትዮጵያ የሔዱት ታዳጊዎች ካረፉበት ትምሕርት ቤት ሳያሳውቁ በመውጣት መሰወራቸውን የስዊድን ፖሊስ አስታውቋል።እግር ኳስ ተጫዋቾቹ ወደ ኢትዮጵያ እንዳልተመለሱ ያረጋገጠው ፖሊስ፤ በራሳቸው ፍላጎት ጠፍተው ሊሆን እንደሚችል አመላክቷል።
በጉዳዩ ዙርያ ምላሽ የሰጠው ፌደሬሽኑ የቡድኑ አባላት መጥፋት እንዳሳዘነው እና ታዳጊዎቹ በመሰል ውድድሮች ላይ በራሳቸው ጥረት በሚያገኙት እድል ወደ ውድድሩ ማምራታቸውን አሳውቋል።
በመሆኑም ታዳጊዎቹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የወከሉ አለመሆኑን እየገለፅን በአንዳንድ አካላት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት እንደሆኑ እየተገለጸበት ያለው መንገድ ትክክል አለመሆኑን እናሳውቃለን ብሏል ፌደሬሽንኑ።
​ፖሊስ የጠፉት ታዳጊዎች ዕድሜያቸው ከ14 እስከ 17 ዓመት የሆኑ ወጣቶች ሲሆኑ፣ ከእነሱ ጋር አንድ ወይም ከዚያ በላይ የቡድን መሪዎች አብረው ጠፍተዋል ብሏል። ይህ የታወቀው በውድድሩ የመጨረሻ ቀን ሲሆን ያረፉበት ትምህርት ቤት አስተዳዳሪ አባላቱ ያለ ምንም ማስታወቂያ ለቀው መሄዳቸውን ካረጋገጠ በኋላ ለፖሊስ ማሳወቁም ተዘግቧል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2