የ«ሁሉ ስፖርት» የፈቃድ ስረዛ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ተሻረ፤ አገልግሎቱ ግን አሁንም ታግዷል​የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኢት…

- Advertisement -
Sidebar AD
የ«ሁሉ ስፖርት» የፈቃድ ስረዛ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ተሻረ፤ አገልግሎቱ ግን አሁንም ታግዷል
​የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት እና የገቢዎች ሚኒስቴር በ«ሁሉ ስፖርት» ላይ አስተላልፈውት የነበረውን የንግድ ፈቃድ ስረዛ ውሳኔ በሙሉ ድምፅ ሻረ። ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን የሻረው ተቋማቱ የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት ሕግን ሳይከተሉ እና የተቋሙን የመሰማት መብት ጥሰው ፈቃድ መሰረዛቸውን በመግለፅ ነው።
​መንግሥት ድርጅቶቹ ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ግብር ሰውረዋል ቢልም፣ ፍርድ ቤቱ ይህ በወንጀል ሕግ የሚታይ እንጂ በደፈናው ለአስተዳደራዊ ፈቃድ ስረዛ ምክንያት ሊሆን አይችልም ብሏል።
​ሆኖም የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በውሳኔው ላይ ይግባኝ ማቅረቡን ተከትሎ፣ የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ አፈጻጸም ከሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ቀናት እንዲታገድ ተደርጓል።
በመሆኑም ጉዳዩ በጠቅላይ ፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ «ሁሉ ስፖርት» ወደ ሥራ አይመለስም።
​ይህ በእንዲህ እንዳለ የሎተሪ አገልግሎቱ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ሕጋዊ ፈቃድ ያለው ምንም ዓይነት የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ድርጅት እንደሌለ አስታውቋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2