የኒውዮርክ ከንቲባ የአፍሪካ ልጅ መሆኔ ያኮራኛል አሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የኒውዮርክ ከተማ ከንቲባ ዞህራን ማምዳኒ አፍሪካዊ ማንነታቸውና ያደጉበት አካባቢ የዓለም አመለካከታቸውን በመቅረጽ ረገድ ከፍተኛ ሚና መጫወቱን ገልጸዋል።

በኡጋንዳ ካምፓላ ተወልደው በስድስት ዓመታቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ ደቡብ አፍሪካ ያመሩት ማምዳኒ ከሁለት ዓመታት ቆይታ በኋላም ወደ አሜሪካ በመዛወር እዚያው አድገው ወደ ፖለቲካው ዓለም ገብተዋል።

ከንቲባው ከ‘ዘ ሩት’ ጋር ባደረጉት ቆይታ በአፍሪካና በአሜሪካ ያሳለፉት የሕይወት ጉዞ የዛሬውን እሴቶቻቸውንና ምልከታቸውን አሁንም ድረስ እንደሚያንጸባርቅ ገልጸው “የአፍሪካ ልጅ በመሆኔ እጅግ እኮራለሁ” ሲሉ አፍሪካዊ ማንነታቸውን በኩራት ተናግረዋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: