ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም እና ለጤና ምርምር የተተከለው አረንጓዴው ተስፋ

- Advertisement -
Sidebar AD


‎#Ethiopia | ​የጤና ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በመተባበር ባካሄደው የችግኝ ተከላ መርሐግብር በቢሾፍቱ አካባቢ ከሰባት ሄክታር በላይ መሬት ላይ ለምግብነት እና ለወደፊት የጤና ምርምር የሚውሉ ከአምስት ሺህ በላይ የሚጠጉ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተተክለዋል።

‎በዕለቱ የተገኙት የአርማወር ሐንሰን ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ፣ በሀገራችን የሚገኙ መድኃኒትነት ያላቸው እጽዋት ከመጥፋት እንዲጠበቁና በምርምር እንዲደገፉ ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አስገንዝበዋል።

‎​ኢንስቲትዩቱ ከዩኒቨርሲቲዎች እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ሕዝቡ ለህክምና የሚጠቀምባቸውን እጽዋት የመመዝገብ፣ የማጥናት እና የመጠበቅ ሥራዎችን አጠናክሮ መቀጠሉን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

‎በተለይም በሶማሌ ክልል እና በሌሎች አካባቢዎች እየተካሄዱ ያሉ ሰርቬዮች የኢትዮጵያን የበለጸገ የእጽዋት ዕውቀት ለማዳን ትልቅ ፋይዳ እንዳላቸው ተመላክቷል።

‎አርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት በግቢው ውስጥ ከሁለት መቶ በላይ መድኃኒትነት ያላቸውን እጽዋት በመሰብሰብ ለምርምር ምቹ የሆኑ የዕፅዋት ማቆያ ቦታዎችን እንዳቋቋመና ይህ መልካም ተሞክሮም በመንግሥት ተቋማትና በትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲስፋፋ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል።
‎ጌትነት ተመስገን
‎📷 ከበደ መክብብ

‎Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

‎#getutemesgen #getu #ጌጡ #ARRI #GreenLegacy #HealthResearch #Ethiopia #MedicinalPlants #ClimateAction



‎​







Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: