”ማንበብና መጻፍ”

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እየተካሄደ በሚገኘው የ‘ንባብ ለሕይወት’ የመጻሕፍት አውደርዕይ ላይ በኪነ ጥበቡ ዓለም ትልቅ ስም ያላቸው ሁለቱ “ፀሐዮች” ደምቀዋል።

በዕለቱ መድረኩን በክብር እንግድነት ተወዳጁ ድምፃዊ ፀሐዬ ዮሐንስ ዘመን ተሻጋሪ የሆነውን “ማንበብና መጻፍ” የተሰኘውን ዜማውን በልዩ ብቃት በመጫወት ሕፃናትን ጨምሮ ታዳሚውን በደስታ ከመቀመጫው አስነስቷል።

​በመርሃ ግብሩ ማጠቃለያም በኢትዮጵያ ሴት ደራሲያን ታሪክ በረዥም ልቦለድ ዘርፍ ፋና ወጊ ፥የሆነችው አንጋፋዋ ደራሲ ፀሐይ መላኩ ለድምፃዊ ፀሐዬ ዮሐንስ የምስጋና ሰርተፊኬት በክብር አበርክተዋል።

የመጻሕፍት አፍቃሪዎችን እያስተናገደ የሚገኘው የ‘ንባብ ለሕይወት’ አውደርዕይ እስከ ሐምሌ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በኤግዚቢሽን ማዕከል የሚቀጥል ይሆናል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1