#Ethiopia | ከሞሮኮ የተነሱ ከ50,000 በላይ ስደተኞች ስፔንን በሰአታት ውስጥ በሰው ማዕበል ያጥለቀለቁ ሲሆን ይህም የስፔን መንግስትን አስደንግጧል።
የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ድርጊቱ የስፔን ግዛት አንድነትን የሚጥስ መሆኑን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለው የመንግስታቸውን ሙሉ አቅም በመጠቀም የከተማዋን እና የነዋሪዎቿን ደህንነት እንደሚያረጋግጡ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህ ክስተት ስደተኞችን የሚያሸጋግሩ ህገ ወጥ ቡድኖችን ወቅሰዋል።
በሰአታት 50,000 የሚጠጉ ስደተኞች ከሞሮኮ በመነሳት የስፔን ግዛት የሆነችውን ታሪካዊቷን ሴኡታ ከተማ አጥለቅለውታል።
ወደ ግዛቷ ለማለፍ የሞከሩ ቢያንስ 57 ስደተኞች ህይወታቸው ማለፉም ተገልጿል።
ክስተቱ በስፔን መንግስት ላይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውጥረት የፈጠረ ሲሆን ከአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራትም ጠንካራ ትችት እያስተናገደ ይገኛል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Spain #emigrates
#pedrosanchez
Source: GetuTemesgen








No comments yet.