በምክክር ሂደቱ የቀረቡ የአጀንዳ ምክረ ሀሳቦች በ75 በመቶ አባላት ተቀባይነት ካገኙ ከመግባባት እንደተደረሰ ጠቋሚ ነዉ የተባለ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በምክክር ሂደቱ የቀረቡ የአጀንዳ ምክረ ሀሳቦች በ75 በመቶ አባላት ተቀባይነት ካገኙ ከመግባባት እንደተደረሰ ጠቋሚ ነዉ የተባለለት የምክክር ምዕራፍ በመጪዉ ሰኞ ይጀመራል ተባለ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በባለፉት ሁለት ቀናት 250 ተመካካሪዎች በቡድን በመከፋፈል ዉይይት ሲያደርጉ መቆየታቸዉን ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ  አሳዉቋል።
በዚህ የምክክር ምዕራፍ የተጀራጁ ምክረ ሀሳቦች 5መቶ አባላት ወዳሉት ቀርበዉ ፤ እነዚህ የ5 መቶ አባላት ተመካካሪዎች ቡድን  ለውሳኔ መግባቢያ ሀሳብ ያደራጁታል ተብሏል።
እንደ ኮሚሽኑ መረጃ 5መቶ አባላት ያሏቸው ተመካካሪ ቡድኖች እያንዳንዳቸው በአንድ አጀንዳ ላይ የሚወያዩ ሲሆን፤በአጀንዳው ላይ ከመግባባት ደረሰ የሚባለው በዉይይቱ  የመነጩ የመፍትሄ ሀሳቦች በ75 በመቶ አባላቱ ከመግባባት የተደረሰባቸው ወይም ተቀባይነት ያገኙ እንደሆነ ነው።
ሌላዉ የምክክሩ የውሳኔ አሰጣጥ አካል የሆነው አካሄድ ከክልል እና ከፌደራል አባላት ተመርጠዉ የሚዋቀረዉ የክልላዊ ጉባኤ ሲሆን፤በዛሬዉ ዕለት 330 ተወካዮች እንደተመረጡ ኮሚሽኑ በሰጠዉ መግለጫ ተናግሯል።
12 ክልሎች እና 2 ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም የፌደራል ተቋማት ከእያንዳንዳቸው 22 ተወካዮች ተወጣጥተው የተዋቀረ ቡድን መሆኑን የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ ገልፀዋል።
በዚህ ቡድን 70% ድምጽ ባለማግኘቱ ውድቅ በተደረገ የአጀንዳ የምክር ሀሳብ ላይ ቢያንስ ሶስት ክልሎች ቅሬታ ያቀረቡ እንደሆነ ያንን የሚፈቱበት አግባብ የሚኖር ነዉ ተብሏል። በቀደሙት የድምፅ አሰጣጥ ሂደቶች 70 በመቶ ድምጽ ማግኘት ሳይችል የቀረ የአጀንዳ ምክረ ሀሳብ በዚህ ቡድን በድጋሚ ታይቶ የሚጠበቀውን ዝቅተኛ የ70 በመቶ መስፈርት ካሟላ ወደ ሚቀጥለው ምዕራፍ የሚሸጋገር ይሆናል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1