#Ethiopia | በእ.ኤ.አ. ጁላይ 22 ቀን 1899 በሚዙሪ ግዛት የተፈጸመው የ19 ዓመቱ ወጣት ፍራንክ ኤምብሪ ግድያ፣ በታሪክ ውስጥ እጅግ አሰቃቂና ህግ አልባ ከሆኑ የደቦ ግድያዎች አንዱ ሆኖ ይጠቀሳል።
ወጣቱ ፍራንክ ዊሊ ዶገርቲ የተባለች የ12 ዓመት ነጭ ልጅ ላይ ጥቃት ፈጽሟል በሚል ተከስሶ ጉዳዩ በህግ ለመታየት ወደ ፍርድ ቤት በመወሰድ ላይ እያለ ነበር በልጅቷ አባት በተመራ ቁጣ የተሞላ የነጮች ስብስብ የታገተው።
ታጋቹ ወጣት ጥፋቱን እንዲያምን ቢጠየቅም አምኖ ባለመቀበሉ ምክንያት፣ ልብሱን አውልቀው በማሰር 103 ጊዜ በጅራፍ የገረፉት ሲሆን በቦታው የተሰበሰቡ ከ3 ሺህ በላይ ሰዎችም ድርጊቱን በደስታ እየደገፉና ፎቶግራፍ ያነሱ ነበር።
ፍራንክ ከአሰቃቂው ስቃይ በኋላ ጥፋተኛ ነኝ ለማለት ቢገደድም አጋቾቹ አካሉን ካጎደሉ በኋላ በዛፍ ላይ ሰቅለው ህይወቱን አጥፍተዋል።
በወቅቱ የገዳዮቹንና የተመልካቾቹን ፊት በግልጽ የሚያሳዩ በርካታ ፎቶግራፎች የተነሱ ቢሆንም፣ ለዚህ አሰቃቂ የነፍስ ግድያ ወንጀል አንድም ሰው ለፍርድ ሳይቀርብና ሳይታሰር ቀርቷል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.