አሜሪካ የፈፀመችው አሳፋሪ ድርጊት ተጋለጠ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካኝነት ተዘጋጅቶ የቀረበው የተሳሳተ የአፍሪካ ሀገራት ካርታና የቀረበው መረጃ በዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ተጋለጠ።

በብራዚል ሪዮ ዲ ጃኔሮ እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የእርዳታ ጉባኤ ላይ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ያቀረበው መረጃ የአፍሪካ ሀገራትን የማይወክል ካርታና መረጃ አቅርቧል።

በምስል ተቀናብሮ ለእንግዶች በቀረበው ካርታ ላይ ናይጄሪያ የባህር በር የሌላት ሀገር ሆና በሰሃራ በረሃ ውስጥ እንደምትገኝ መድቧታል።

እንደዚሁም ሞዛምቢክ በምስራቅ አፍሪካ ወይም አፍሪካ ቀንድ የመደባት ሲሆን አይቮሪኮስት ከአህጉሩ ተቃራኒ አቅጣጫ ላይ የምትገኝ ሀገር ብሏታል።

ቪዲዮው እና በስላይዱ የቀረበው ካርታ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ አማካኝነት የተሰራ መሆኑን ተረጋግጧል።

በስብሰባው ላይ የተገኙ የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች እና የጤና ባለሙያዎች የካርታውን ምስል በማንሳት በማህበራዊ ሚዲያ አሰራጭተውታል።

ድርጊቱ ለአፍሪካ ሀገራት የተሰጠው አነስተኛ ትኩረት የሚያሳይ እና የሚያሳፍር ተግባር ሲሉ ኮንነውታል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተፈጠረው ስህተት ሙሉ ኃላፊነት እንደሚወስድ አስታውቋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Usforeignminister
#Africa #maps #Brazil


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: