ዘመናዊቷን ኢትዮጵያ ከአማራና ኦሮሞ ውህደት ውጭ ማየት አይቻልም

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ሀገሪቱን ለመቀየር ፖለቲካውንም ሆነ ኢኮኖሚውን ጎን ለጎን ክፍት ማድረግ አስፈላጊ እንደነበር ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲያብራሩም የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ ከአማራና ከኦሮሞ ሕዝቦች ጥብቅ ውህደትና ትስስር ውጭ ሊታይ አይችልም። የዓድዋ ድልም የዚሁ ታሪካዊ አንድነት ትልቁ ማሳያ ነው፤ አብሮ የመኖር ባህልም የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ እሴት እንደሆነ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል፣ በሀገራችን ስልጣንን በኃይልና በሰው ግድያ ለመያዝ የመሞከር አጥፊ ባህል እንደነበር አውስተዋል። በዚህም የሰኔ 15ቱ ክስተት በለውጡ ውስጥ ትልቅ ሚና የነበራቸውን ሰዎች ያጣንበት የሕመም ጠባሳችን ነው ብለዋል።

ሆኖም ሕዝቡ ለውጡን በሙሉ ልብ የተቀበለ ሲሆን፣ በአንድነትና በትብብር አንዲት ጠንካራ ሀገር መገንባት እንደምንችል በምርጫው ወቅት በተግባር ማረጋገጡን ገልጸዋል።

#PMAbiyAhmed #AMICO #Ethiopia #Medemer #AmharaAndOromo #EthiopianUnity


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: