የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተስፋዬ ቦሩ ታገዱ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | አቶ ተስፋዬ ቦሩ በተደጋጋሚ የሕግና የቁጥጥር መመሪያዎችን ጥሰዋል በሚል ከያዟቸው የሥራ ኃላፊነት እንዲነሱና ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በምንም ዓይነት የፋይናንስ ተቋም ውስጥ በከፍተኛ የአመራርነት ደረጃ እንዳያገለግሉ ዕገዳ ጣለባቸው።

​ማዕከላዊ ባንኩ የጻፈውን ይፋዊ ደብዳቤ ጠቅሶ እንዳመለከተው ይህ ውሳኔ የተላለፈው በግሎባል ባንክ ላይ ከተካሄደው ልዩ ኢንስፔክሽን በኋላ ነው ብሏል ካፒታል ጋዜጣ።

በተደረገው ጥልቅ ፍተሻ በባንኩ የመልካም አስተዳደር፣ የብድር አሰጣጥና አስተዳደር፣ የሰው ኃይል፣ የውጭ ምንዛሪ አሰራር እና አጠቃላይ የፋይናንስ አስተዳደር ላይ በርካታ የሕግና የመመሪያ ጥሰቶች መገኘታቸው ተረጋግጧል።

​የተገኙት ክፍተቶች አሳሳቢነት እንዲሁም አቶ ተስፋዬ ቀደም ሲል በግንቦት 2013 ዓ.ም እና በህዳር 2017 ዓ.ም የተሰጧቸውን የጽሑፍ ማስጠንቀቂያዎች ከግምት በማስገባት ብሔራዊ ባንኩ በሕጉ የተሰጠውን ሥልጣን ተጠቅሞ እርምጃውን ወስዷል።

በዚህም መሠረት ከአሁን ጀምሮ አቶ ተስፋዬ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚንቀሳቀስ በማንኛውም የፋይናንስ ተቋም ውስጥ በቦርድ አባልነት፣ በዋና ሥራ አስፈጻሚነትም ሆነ በሌሎች ከፍተኛ ሥራ አስፈጻሚ ቦታዎች ላይ እንዳያገለግሉ በሙሉ ድምፅ ተከልክለዋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2