#Ethiopia | የጣልያን መንግሥት ከስፔን ጋር ባለው የባሕርና የአየር መንገድ መስመር የሸንገን የነፃ ዝውውር ስምምነትን በጊዜያዊነት በማቋረጥ የድንበር ቁጥጥር ማድረጉን አወጀ።
ይህ አስቸኳይ እርምጃ የሀገሪቱን ብሔራዊ ደህንነት ለመጠበቅና ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመከላከል የተወሰደ ሲሆን በበጋው የቱሪዝም እንቅስቃሴ ላይ የሚፈጥረውን ተጽዕኖ በመቀነስ ላልተወሰ ጊዜ የሚተገበር መሆኑ ተገልጿል።
በተመሳሳይ መልኩ ጣልያን የአውሮፓ ሕብረትን የውጭ ድንበሮች ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት የስፔን ተቋማትን ለመደገፍና የተደቀነውን ችግር በጋራ ለመጋፈጥ ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች።
የጣልያን ጠ/ሚ ጂዮርጂያ ሜሎኒ
አፅንዖት ሰጥተው እንደተናገሩት ድንበርን ማስከበር የዜጎችን ደህንነት ከመጠበቅ ባሻገር ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርንና የወንጀል አውታሮችን በቁርጠኝነት ለመግታት የሚደረግ ወሳኝ እርምጃ ነው።
ሸንገን በመላው አውሮፓ አባል ሀገራት እንድንቀሳቀስ የሚፈቅድልን የቪዛ አይነት ነው።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen








No comments yet.