#Ethiopia | የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የታገዘ ሮቦት በከፍተኛ ትክክለኛነትና ራሱን በራሱ በመምራት የመጀመሪያውን የሐሞት ከረጢት የማውጣት ቀዶ ሕክምና በሞተ አሳማ ላይ በስኬት ማከናወኑን አስታወቁ።
ይህ ስኬት ወደፊት ሙሉ በሙሉ ራሳቸውን ችለው ወደሚሠሩ የቀዶ ሕክምና ሮቦቲክስ ሥርዓቶች በሚደረገው ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ሆኖ ተመዝግቧል።
ይህ ሮቦት የ17 ሰዓታት የሰዎች የቀዶ ሕክምና ቪዲዮዎችን መሠረት አድርጎ በተዘጋጀ ባለ ሁለት ደረጃ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሞዴል የሰለጠነ ነው።
ሞዴሉ የምስል መረጃዎችን ወደ ቃል ትዕዛዞች በመቀየር፣ ትዕዛዞቹን ደግሞ ወደ ተጨባጭና ጥንቁቅ የመሣሪያ እንቅስቃሴዎች በመተርጎም ሥራውን አከናውኗል።
በሂደቱም በስምንት የተለያዩ የሕክምና ሙከራዎች የተሰጡትን 17ቱንም የቀዶ ሕክምና ተግባራት ራሱን በራሱ እያስተማረ በመቶ በመቶ በስኬት ያጠናቀቀ ሲሆን የሰዎች ጣልቃ ገብነትም እጅግ አነስተኛ ነበር።
በሕያዋን ሰዎች ላይ እንዲህ ያሉ ሙሉ በሙሉ ራሳቸውን የቻሉ የቀዶ ሕክምናዎችን ለመተግበር የዓመታት ጊዜ የሚወስድ ቢሆንም የዚህ ሙከራ ውጤት ግን የሮቦቲክስ ሕክምና አስተማማኝነት እየጨመረ መምጣቱን አሳይቷል።
ተመራማሪዎቹ ቀጣዩ እርምጃቸው በሕያዋን እንስሳት ላይ ሙከራ ማድረግ እንደሆነና የረጅም ጊዜ ዓላማቸው ደግሞ የቀዶ ሕክምናዎችን ደህንነትና ትክክለኛነት በመጨመር በሕክምና ባለሙያዎች ላይ የሚፈጠረውን ጫና መቀነስ መሆኑን ገልጸዋል።
የዚህ ጥናት ዝርዝር መረጃ በሳይንስ ሮቦቲክስ የምርምር መጽሔት ላይ ታትሞ ይፋ ሆኗል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen








No comments yet.