ጄጄ ግሩፕ በኡራኤል ባለ 12 ወለል ህንፃ ግንባታ ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አስጀመረ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja:- በኮንስትራክሽን እና ሪል እስቴት ዘርፍ የተሰማራው ጄጄ ግሩፕ (JJ Group)፣ በኡራኤል አደባባይ አካባቢ ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቅ ባለ 12 ወለል ባለብዙ አገልግሎት ህንፃ ግንባታ በይፋ ማስጀመሩን በዛሬዉ እለት አስታወቀ።

ህንፃው ለንግድ፣ ለቢሮ እና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል ሲሆን እስከ ሁለት የከርሰ-ምድር (Basement) እና 12 ወለሎችን (G + 12) የያዘው ይህ ህንፃ፣ ከ10 እስከ 47 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው ከ60 እስከ 70 የሚደርሱ የንግድ ሱቆች፣ በ4ኛው ወለል ላይ የተዘጋጁ የቢሮ ቦታዎች እንዲሁም 31 ባለ ሁለት መኝታ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል።

ህንፃው ለተረጋጋ የመኖሪያ alalar™ ሲባል ለንግድና ለመኖሪያ ክፍሎቹ የተለያየ መግቢያና መውጫ እንዲኖረው ተደርጎ የተዋቀረ እንደሆነም ነዉ የተገለፀዉ።

የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የኢትዮጵያ ሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ጀበል ጀማል እንደገለፁት ድርጅታቸው ባለፉት 13 ዓመታት በዘርፉ በነበረው ልምድ ከ4ዐ በላይ ህንፃዎችንና ፋብሪካዎችን ገንብቶ ማስረከቡን ጠቁመው፣ በቅርቡ ይፋ የሚሆነው የሪል እስቴት አዋጅና ደንብ የገዢዎችንና የአልሚዎችን መብት የሚያስከብር መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ ስራ አስፈፃሚው ገለጻ፣ የንግድ ሱቆቹን በ8 ወራት፣ የመኖሪያ አፓርትመንቶቹን ደግሞ በ2 ዓመታት ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለደንበኞች ለማስረከብ ማቀዱንም ገልፀዋል።

አቶ ጀበል አክለውም “ገንዘብ በዝግ አካውንት ተቀምጦ በስራው እድገት ልክ በባንክና በባለሙያ እየተረጋገጠ የሚለቀቅበት አሰራር መዘርጋቱ በዘርፉ ላይ ታማኝነትን ይፈጥራል” ብለዋል።

በተጨማሪም የፕሮጀክቱን መበሰር ምክንያት በማድረግ በቅድመ-ሽያጭ (Pre-sale) ደረጃ 10 አፓርትመንቶች ብቻ በልዩ ቅናሽ ለገዢዎች መቅረባቸው ተገልጿል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: