#Ethiopia | በቅርቡ በማህበራዊ ገጹ ላይ እግሮቹ መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው ምክንያት ወደ ቱርክ አቅንቶ የህክምና ኦፕራሲዮን ለማድረግ የገንዘብ ድጋፍ ሲጠይቅ የነበረው ወጣት ከተለያዩ በጎ አድራጊዎች ተስፋ ሰጪ ምላሽ እያገኘ ይገኛል።
እንደ ክርስቲያን ቲዮብ ዘገባ ለዚህ ወጣት ህክምና በአጠቃላይ 3.7 ሚሊዮን ብር የሚያስፈልግ ሲሆን እስካሁን ባለው ሂደት 2.5 ሚሊዮን ብሩ በእጁ ይገኛል።
ይሁን እንጂ ለህክምናው የሚጎድለውን 1.2 ሚሊዮን ብር ለማግኘት ወገኖቹ እንዲያግዙት ሲማፀን ቆይቷል።
ይህንን ሁኔታ የተመለከቱትና በበጎ አድራጎት ስራዎቻቸው የሚታወቁት ቄስ ሙሉነህ ታዬ ከሚጠበቀው ቀሪ ገንዘብ ላይ የ25 በመቶውን ወይም የ300 ሺህ ብር ወጪ ለመሸፈን ቃል ገብተዋል።
ይህ የቄስ ሙሉነህ አብነታዊ የደግነት ተግባር የብዙዎች መነሳሳት የፈጠረ ሲሆን ቀሪውን ገንዘብ ለማሰባሰብ ለሚደረገው ጥረት ትልቅ መነቃቃትን ፈጥሯል።
አሁንም ማህበረሰቡ የተለመደውን የትብብር እጁን በመዘርጋት በቀሪነት የሚጠበቀውን የገንዘብ መጠን በሂሳብ ቁጥር 1000276333112 ገቢ በማድረግ የወንድማችንን ህይወት እንድንታደግ ጥሪ ቀርቧል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen








No comments yet.