በሸረሪና ከባድ የተኩስ ልውውጥዛሬ ቅዳሜ ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም ከንጋቱ 11: 45 ጀምሮ በሸረሪና አከባቢ በኢትዮጵያ መከላከ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በሸረሪና ከባድ የተኩስ ልውውጥ‼️
ዛሬ ቅዳሜ ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም ከንጋቱ 11: 45 ጀምሮ በሸረሪና አከባቢ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና እዛ አካባቢ በሚንቀሳቀሱ የትግራይ ኃይሎች መካከል ከባድ ውጊያ መቀስቀሱን ምንጮች ጠቁመዋል።
አርሚ 70 በመባል የሚታወቀው የትግራይ ሰራዊት አንዱ ህዋስ ይንቀሳቀስበታል ተብሎ በሚታወቀው በዚህ ስፍራ የተቀሰቀሰው ይህ ጦርነት፣ በእግረኛ እና በሜካናይዝድም ጭምር የታገዘ ከባድ (full-scale) ጦርነት መሆኑን የጠቀሱት ምንጮች፣ ይህ ክስተት በቅርቡ በተለያዩ የትግራይ ከተሞች በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች እየተመራ ሲካሄድ የቆየውና “ጦርነት ቀስቃሽ” ይዘት ያላቸው መፈክሮች የተስተጋቡበትን ህዝባዊ ኮንፈረንስ መጠናቀቁን ተከትሎ የተቀሰቀሰ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ይሰጣሉ።
ተኩሱ እስካሁን የቀጠለ ሲሆን መድፍን ጨምሮ የከባድ መሳሪያ ተኩስ እንደቀጠለ ነው፣በሽራሮ አቅጣጫ የከባድ መሳሪው ድምጽ እንደመሰማ የአካባቢው ምንጮች ገልፀውልናል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1