በጎሮ ጉሊት አካባቢ መንገድ ላይ ተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋዎች እየደረሱ መሆናቸው ተገለጸ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I በጎሮ ጉሊት አካባቢ በሚገኘው የአስፋልት መንገድ ላይ በተደጋጋሚ በሚከሰቱ የትራፊክ አደጋዎች ምክንያት የሰው ህይወት አልፎ በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ። ነዋሪዎቹ የሚመለከተው አካል በአስቸኳይ በፍጥነት መቀነሻ (Speed Breaker) በመስራት የሰዎችን ህይወት እንዲታደግ ጥሪ አቅርበዋል።

​በተለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ አንዲት የአካባቢው ነዋሪ በስሜት ውስጥ ሆና እያለቀሰች እንደገለጸችው፤ ጉዳዩ ምንም ዓይነት ድራማ ወይም ማጋነን የሌለበትና በአካባቢው የሚኖሩ ነዋሪዎች በሙሉ የሚያውቁት እውነተኛ ስቃይ ነው ብላለች። ነዋሪዋ ወደ ሰፈሩ ከገባችበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ በተደጋጋሚ ጊዜያት አስቃቂ የመኪና አደጋዎች ሲከሰቱ መመልከቷን ተናግራለች።

​አደጋው በየጊዜው የበርካታ ወገኖችን ህይወት እየቀጠፈና አካል እያጎደለ የሚገኝ በመሆኑ ጉዳዩ የሚመለከተው የመንግስት አካል ወይም የሚመለከታቸው አካላት በአስፋልቱ ላይ ፍጥነት መቀነሻ በመስራት ተጨማሪ አደጋዎችን እንዲከላከሉ ተጠይቋል። በተጨማሪም ህብረተሰቡና አሽከርካሪዎች በአካባቢው በሚያሽከረክሩበት ወቅት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪዋን አስተላልፋለች።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: