* አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ፦ የሰዎች ህመም የሚሰማቸው፣ ተስፋን በተግባር የሚተረጉሙት ስራ ፈጣሪ
“Life’s most persistent and urgent question is, ‘What are you doing for others?’”
(የህይወት ዘወተር እና አጣዳፊው ጥያቄ፦ ‘ለሌሎች ሰዎች ምን እያደረግክ ነው?’ የሚለው ነው።)
— ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር
#Ethiopia | በማህበረሰብ ውስጥ የሚታዩ ክፍተቶችን አይቶ ከመቆጨት ይልቅ የመፍትሔ አካል ለመሆን መነሳት የትልልቅ ሰዎች መለያ ባህሪይ ነው። በትውልደ ኢትዮጵያዊው ስራ ፈጣሪ አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ ዘንድም የሚታየው ይህ ህያው እውነት ነው፤ ጥበብን፣ የበጎ አድራጎት መንፈስን እና ዘመናዊ የህክምና አገልግሎትን በማስተሳሰር በሀገራችን ልዩ የለውጥ አሻራ በማስቀመጥ ላይ ይገኛሉ።
የተድላ አምቡላንስ መወለድ፦
የህይወት አድን አገልግሎት ራዕይ
አቶ ሳሚ ካህሳይ በሀገራችን በህክምና ትራንስፖርት ዘርፍ ያለውን ትልቅ ክፍተት በጥናት በመረዳት ነው “ተድላ አምቡላንስን” ወደ ስራ ያስገቡት። በተለይም አካል ጉዳተኞች፣ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት (ኦቲዝም) ያለባቸው፣ የዳያሊሲስ ህመምተኞች እና አረጋውያን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሚያጋጥማቸውን የእንቅስቃሴ እና የትራንስፖርት እንግልት በመመልከት፣ ደረጃውን የጠበቀና ዘመናዊ የድንገተኛ እና ድንገተኛ ያልሆነ የህክምና መጓጓዣ አገልግሎት እንዲመሰረት አድርገዋል።
ድርጅቱ ከንግድ ስራ በላይ የማህበረሰብ አለኝታነትን መርሁ በማድረግ፦
* ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን ያቀረበ፣
* በገንዘብም ሆነ በአገልግሎት ደረጃ አቅም የሌላቸውን ለመደገፍ የተጋ፣
* ለሁሉ አቀፍ ተደራሽነትና ለዜጎች ክብር የቆመ ተቋም ሆኖ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።
“The best way to find yourself is to lose yourself in the service of others.”
(ራስህን ለማግኘት የሚቻለው የተሻለው መንገድ በሌሎች አገልግሎት ውስጥ ራስህን ስትሰጥ ነው።)
— ማሃትማ ጋንዲ
“ማንም የላት”፦
ጥበብ ለሰብአዊነት እና ለማህበራዊ ንቅናቄ
አቶ ሳሚ ከስራ ፈጣሪነታቸው ባሻገር፣ ጥበብ ለማህበራዊ ለውጥ ያላትን ትልቅ ሀይል በመረዳት ከ1.2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ “ማንም የላት” የተሰኘውን ታሪካዊ የኅብረት ዜማ ፕሮዲዩስ አድርገዋል።
ይህ ስራ በግጥም ናትናኤል ግርማቸው፣ በዜማ አህመድ ተሾመ (ዲንቢ)፣ በቅንብር ታምሩ አማረ (ቶሚ) እንዲሁም በዳይሬክቲንግ ነፃዓለም አብዲ የተቃኘ ሲሆን፤ ድምፃውያን ማስተዋል እያዩ፣ ሄዋን ገብረወልድ፣ ሀና ግርማ እና አብርሃም በላይነህ (ሻላዬ) ድምፃቸውን ሰጥተውበታል። ከ50 በላይ የሙያ አጋሮች የተሳተፉበት ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት፣ ህብረተሰቡን ስሜታዊ ጉዳት ውስጥ ሳይከት በደማቅ ቅንብር የችግሩን አሳሳቢነትና የለውጥ አስፈላጊነት ያሳያል።
አካል ጉዳተኝነት የችግር ምንጭ ሳይሆን፣ እንደ ማህበረሰብ የፈጠርነው የመዳረሻ እና የትራንስፖርት እጥረት ዋናው ክፍተት መሆኑን ማሳወቅ ነው። “ማንም የላት” የሚለውን ስሜት “እኛ አለንላት!”በሚል አዎንታዊ ምላሽ ለመተካት ያለመ ማህበራዊ ንቅናቄ ነው።
አቶ ሳሚ ካህሳይ እና ድርጅታቸው ተድላ አምቡላንስ ቃላቸውን በተግባር በማስመስከር፤ ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ በተደረገ ስነ-ስርዓት፦የሙዚቃ ቪዲዮውን ገቢ፦ በሰይፉ ኦን ኢቢኤስ (Seifu on EBS) የዩቲዩብ ቻናል ተለቆ የሚሰበሰበው ሙሉ ገቢ ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማዕከል እንዲሆን አስረክበው ነበር።
በርካታ ዊልቸሮች፣ ዘይት፣ ላርጎ እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለመቄዶንያ መስራች ለዶ/ር ቢንያም በለጠ በአካል አስረክበዋል።
ተድላ አምቡላንስ ለማንኛውም ሰዓት ለመቄዶንያ ማዕከል ነፃ የአምቡላንስ አገልግሎት ለመስጠት በይፋ ቃል ገብተዋል።
የአቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ ህልም በዋና ከተማው አዲስ አበባ ብቻ የተገደበ አይደለም። በክልሎች፣ በገጠራማ አካባቢዎች እና ክፍለ ሀገራት የሚኖሩ፣ አማራጭ ያጡ ዜጎች ዘንድ ይሄው ዘመናዊና የተከበረ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲደርስ ከመንግስት እና ከተለያዩ አካላት ጋር በትስስር ለመስራት አቅደዋል።
“No one has ever become poor by giving.”
(መስጠት ማንም ሰው ደሃ አያደርግም።)
— አን ፍራንክ
አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ በስራ ፈጠራቸው ሀገራዊ ክፍተትን የደፈኑ፣ በጥበብ ስራቸው የማህበረሰብ ህሊናን ያነቁ፣ በበጎ አድራጎታቸው ደግሞ የብዙዎችን እምባ ያበሱ የዘመናችን አርአያ ናቸው።
ተድላ አምቡላንስ “ሕይወትን ለማስቀጠል እየመጣን ነው!” በሚለው መሪ ቃሉ፣ የብዙዎችን ህይወት የመታደግ እና ተስፋ የመንዛት ታላቅ ሀገራዊ አገልግሎቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።
መደምደሚያ
አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ ከ 27 ዓመታት ሰድት በኋላ አገር ቤት መጥተዋል። የእናት ሀገር ኢትዮጵያ ጥሪ ተቀብለው “እናቴ፤
የሀገር ጥሪን የመለሰ የዲያስፖራ ተሳትፎ፦ ህልምን በሀገር ላይ መተርጎም እንደነሳሚ ነው።
“Ask not what your country can do for you — ask what you can do for your country.”*
(ሀገሬ ምን አደረገችልኝ ሳይሆን፣ እኔ ለሀገሬ ምን አደረግሁ ብለህ ጠይቅ።)
— ጆን ኤፍ. ኬኔዲ
አቶ ሳሚ ካህሳይ በምዕራቡ ዓለም (በአሜሪካ) ያካበቱትን የሙያ ልምድ፣ እውቀትና ሀብት ይዘው ወደ ሀገራቸው በመመለስ በህክምናና በትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩት በምክንያት ነው። መንግስትና የሀገር ጥሪ ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ያቀረቡትን ጥሪ መሰረት በማድረግ፣ በውጭ ሀገር ያዩትን ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥና ህልማቸውን በሀገራቸው ምድር ላይ ተግባራዊ አድርገዋል።
ይህ እርምጃቸው ክፍተቶችን በመሙላት ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረከተ ሲሆን፤ ሌሎች በውጭ ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንም በየተሰማሩበት የሙያ ዘርፍ መጥተው ሀገራቸውንና ህዝባቸውን እንዲያገለግሉ ትልቅ ማነቃቂያና መንገድ ጠራጊ አርአያ የሚሆን ነው።
እናንት ያገሬ ልጆች
ግልጽነት ለዘላለም ይኑር!
መሥራት ጀግንነት ነው፤ ማድነቅ ደግሞ ጀግንነት ነው!
ለሥራቸው፤ ለሰበአዊነታቸው እጅ እንነሳለን!
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
“ሕይወትን ማዳን፤ የመጀመሪያ ቅድሚያችን!”
– ተድላ አንቡላንስ
📞 ለአስቸኳይ ጥሪዎች 24 ሰዓት፣ 7 ቀናት ዝግጁ
☎️ +251 985 585 888
📞 8558
ይከተሉን፦
Facebook: https://www.facebook.com/Tedlaambulance
Instagram: https://www.instagram.com/invites/contact/?utm_source=ig_contact_invite&utm_medium=copy_link&utm_content=yh2my9l
Telegram: https://t.me/tedlaambulanceservice
Tiktok :- tiktok.com/@tedlaambulance



Source: GetuTemesgen









No comments yet.