#Ethiopia | በካፋ ባህል፣ ታሪክ እና የማህበረሰቡ የኑሮ ዘይቤ ላይ የሚያተኩረው “ኮከል ማሚቶ” የተሰኘ የኢትኖግራፊ መጽሐፍ እሁድ፣ ሐምሌ 26 / 2018ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት በቦንጋ ከተማ በICT አዳራሽ በይፋ ይመረቃል።
መጽሐፉ በአምስት ዋና ዋና ክፍሎች የተደራጀ ሲሆን፣ የካፋን ማህበረሰብ ከሙዚቃ፣ ከመናፍስት እምነቶች፣ ከጦረኝነት ባህል፣ ከተፈጥሮ ጋር ካለው ትስስር እንዲሁም ከአዕዋፋት ጋር የተያያዙ በርካታ ባህላዊና ማህበራዊ ጉዳዮችን በሰፊው ይዳስሳል።
በባህል፣ በማህበረሰብ እና በነባር የኑሮ ትስስር ላይ የሚያተኩሩ የኢትኖግራፊ ሥራዎች በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እምብዛም በማይገኙበት ሁኔታ፣ “ኮከል ማሚቶ” በዘርፉ አዲስ አቅጣጫ የሚከፍት እና ለቀጣይ የምርምርና የጽሑፍ ሥራዎች መነሻ የሚሆን መጽሐፍ እንደሚሆን ተስፋ ተጥሎበታል።
የመጽሐፉ ምረቃ ሥነ ሥርዓት የባህል ባለሙያዎችን፣ የሥነ ጽሑፍ ወዳጆችን፣ ተመራማሪዎችን እና የካፋ ባህልን ለማወቅ ፍላጎት ያላቸውን ሁሉ እንዲታደሙ ጥሪ ያቀርባል።
Source: GetuTemesgen









No comments yet.