የቀድሞዋ የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር አምባሳደር ስንቅነሽ እጅጉ አረፉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | አዲስ አበባ፦ የቀድሞዋ የኢፌዲሪ የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር አምባሳደር ስንቅነሽ እጅጉ ወልደ ማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ማለፋቸውን የማዕድን ሚኒስቴር አስታውቋል።

አምባሳደር ስንቅነሽ በቀድሞው የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ከባለሙያነት እስከ አመራር ደረጃ ድረስ ያገለገሉ ሲሆን፣ በኋላም በቀድሞው የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እንዲሁም ከ2003 እስከ 2006 ዓ.ም. ድረስ የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል።

የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 6፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ ገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸውና አድናቂዎቻቸው በሚገኙበት ይፈጸማል።

የማዕድን ሚኒስቴር በመግለጫው በአምባሳደር ስንቅነሽ እጅጉ ህልፈተ ሕይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝቷል።





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1