የአርሶ አደሩን ድካም የሚያቃልል አዲስ ማሽን በደብረ ታቦር ተፈጠረ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የደብረ ታቦር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተመራቂዎች በረከት ፀጋው እና ቤዛዊት ሲሳይ ሰብልን በአንድ ጊዜ የሚወቃና የሚያበጥር አዲስ የግብርና ማሽን በመፍጠር ትኩረት ስበዋል።

አዲሱ ማሽን አርሶ አደሮች እህል ለመውቃት ይጠቀሙበት የነበረውን ብዙ የሰው ኃይልና የእንስሳት ጉልበት የሚተካ ሲሆን፣ ሥራውን በሁለት ሰዎች ብቻ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ያስችላል። ይህም የምርት ሂደቱን በማፋጠን የሥራ ወጪን ለመቀነስ እንደሚያግዝ ይጠበቃል።

ወጣቶቹ ከትምህርታቸው ጎን ለጎን ይህን ፈጠራ ማበልጸጋቸው ለሌሎች ወጣቶች በፈጠራና በራስ አቅም ሥራ ፈጠራ ረገድ አርአያ ሆኗል።

የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደርም ለፈጠራው ቀጣይ እድገት የቦታ፣ የሼድ እና የብድር ድጋፍ በማድረግ ከፈጣሪዎቹ ጎን እንደሚቆም አስታውቋል።

አሚኮ (AMICO)

#Ethiopia #DebreTabor #Innovation #AgriTech #TVET #EthiopianYouth #Agriculture #ግብርና #ፈጠራ




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: