የጥንዶቹ ውድ የአልማዝ ቀለበት

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የእግር ኳስ ኮከቡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና እጮኛው ጆርጂና ሮድሪጌዝ የጋብቻ ሥነ ሥርዓታቸውን ሊፈጽሙ ነው የሚለው ወሬ በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት ስቧል።

ጥንዶቹ በቅርቡ በማጆርካ የቅንጦት ጀልባ ላይ እንዲሁም በግል ጄታቸው ውስጥ ሲሳፈሩ ያጠለቁት ውድ የአልማዝ ቀለበት ምክንያት የሰርጉ ወሬ የበለጠ እንዲጋጋል አድርጎታል።

ጥንዶቹ ተመሳሳይ ዲዛይን ያላቸውን እጅግ ውብና ውድ የአልማዝ ቀለበት አድርገው በማህበራዊ ገጻቸው ላይ ለቀዋል።

ጥንዶቹ ያጠለቁት የአልማዝ ቀለበት ውድ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ዋጋውም ከ2 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሆነ ተገልጿል።

የጋብቻ ወሬው ከተሰራጨ በኋላ የፖርቹጋል መገናኛ ብዙኃን የሰርግ ጥሪ ወረቀት ተሰራጭቷል ብለዋል።

ሆኖም ከጥንዶቹ የቅርብ ሰዎችና ከየመዝናኛ መጽሔቶች የተገኘ መረጃ ግን ጥንዶቹ በአሁኑ ወቅት ከቤተሰቦቻቸው ጋር እረፍታቸውን እያሳለፉ እንደሆነ ገልጸዋል።

እንደዚሁም ይፋዊ የሰርግ ቀን እንደልተቆረጠ ገልፀዋል።

ሮናልዶ እና ጆርጂና እስካሁን በይፋ የሰርጋቸውን ቀን ያላወጁ ቢሆንም በየቀኑ የሚያሳይዋቸው ውድ አልባሳትና ጌጣጌጦች በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ደጋፊዎቻቸው ዘንድ መነጋገርያ ርዕስ ሆነዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Ronaldo #GeorginaRodriguez
#Bride


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1