ጦርነት ተከፍቶብናል:-ህወሓት”የትግራይ ህልውና በብልፅግና መቃብር ላይ ይወሰናል” በሚል ስብሰባ ሲያካሂድ የከረመው ህወሓት በም…

- Advertisement -
Sidebar AD
ጦርነት ተከፍቶብናል:-ህወሓት‼️
“የትግራይ ህልውና በብልፅግና መቃብር ላይ ይወሰናል” በሚል ስብሰባ ሲያካሂድ የከረመው ህወሓት በምዕራብ ትግራይ ተኩስ ተከፍቶብናል ብሏል።
ሙሉ የመግለጫው ትርጉም👇👇
“የፌደራል መንግሥቱ የትግራይን ሕዝብ ለማጥፋት ሲያካሂድ የቆየውን ሁለንተናዊ ከበባ እና እገዳ፣ በድሮን እና በተላላኪ ታጣቂዎቹ ሲፈጽም የቆየውን ጥቃት ወደ ከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ፣ ዛሬ ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. ከማለዳው ጀምሮ በምዕራባዊ ትግራይ ዞን በሸረሪ አቅጣጫ ግልጽ ጦርነት ጀምሯል።
የፕሪቶሪያው ስምምነት ከተፈረመ በኋላ እንኳ የትግራይን ሕዝብ ለማንበርከክ እና ለመበታተን ካለው ከፍተኛ ፍላጎት ተነሥቶ የተለያዩ ከበባዎችን፣ እገዳዎችን እና ወታደራዊ ዝግጅቶችን ሲያደርግ ቆይቶ፤ ድጋሚ ትግራይን ለመውረር እና ሕዝቡን ለማጥፋት ተነሳሽነት ወስዶ ጦርነት ከፍቶብናል።
​ስለሆነም በሀገር ውስጥ እና በውጭ የምትኖሩ የትግራይ ሕዝብ፣ ሁላችሁም የትግራይ የጸጥታ ኃይሎች፣ ብሔራዊ ኃይሎች እና የትግራይ ታጋዮች፣ የትግራይ ሲቪል ማኅበራት፣ የትግራይ ሃይማኖት ተቋማት እና ሌሎች የሚመለከታችሁ አካላት በሙሉ ብሔራዊ ህልውናችንን ለማረጋገጥ በሚደረገው ፍትሐዊ ትግል “ለብሔራዊ ጥፋት ፈጽሞ አንበረከክም! ብላችሁ ዛሬም እንደ ትናንቱ ተአምራዊ ታሪክ ለመሥራት እንድትዘጋጁ እያቀረብን፤ የተጀመረውን ድጋሚ ወረራ እና ጥፋት የሚመለከቱ የሁኔታዎች እድገት በየጊዜው በሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊው ማብራሪያ እና መግለጫ የሚሰጥበት መሆኑን እናስታውቃለን” ብሏል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: