ሳውዲ አረቢያን ጨምሮ በርካታ የአረብ ሀገራት በጋዛ የተደረሰውን ስምምነት እንደሚደግፉ ገለጹ

- Advertisement -
Sidebar AD

የተለያዩ የአረብ ሀገራት በጋዛ የተደረሰውን ስምምነት በበጎ ሁኔታ እንደሚቀበሉ የገለጹ ሲሆን፣ እስራኤልም ግዴታዎቿን እንድትወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

ሳውዲ አረቢያ በጋዛ የተደረሰውን ስምምነት በደስታ እንደምትቀበል ገልጻ፤ እስራኤል ጦሯን ከጋዛ ሙሉ በሙሉ እንድታስወጣ፣ ሰብአዊ እርዳታዎች ያለማቋረጥ እንዲገቡ እና የሰላም እቅዱ ደረጃዎች በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆኑ ጠይቃለች።

ኳታር በበኩሏ እስራኤል በስምምነቱ መሠረት ግዴታዎቿን እንድትወጣ እና የተኩስ አቁም የመንገድ ካርታው ቀሪ ምዕራፎች ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲደረጉ አሳስባለች።

ዮርዳኖስም በተመሳሳይ የእስራኤል ጦር ከጋዛ ግዛት ሙሉ በሙሉ እንዲወጣ፣ ሰብአዊ እርዳታዎች በዘላቂነት እንዲቀርቡ እና የስምምነቱ ቀጣይ ምዕራፍ እንዲተገበር ጥሪዋን አስተላልፋለች።

የኩዌት መንግሥት በበኩሉ የእስራኤል ጦር መውጣትን፣ የእርዳታ አቅርቦት መቀጠልን እና መልሶ የመገንባት ጥረቶችን ጨምሮ የጋዛው ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን ድጋፉን ገልጿል።

ሀገራቱ ይህን ጥሪ ያቀረቡት በጋዛ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እና በጦርነት የደቀቀውን አካባቢ መልሶ ለመገንባት በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ትኩረት በማድረግ መሆኑ ተገልጿል።

ልዑል ወልዴ



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: