እነዚህ ከላይ በቪዲዮ የምታያቸው ህፃናት በአረብ ሀገር ተሰዳ እረጅም አመት አብራቸው የነበረች ሰራተኛ ኮንትራቷን ጨርሳ ወደ ሀ…

- Advertisement -
Sidebar AD
እነዚህ ከላይ በቪዲዮ የምታያቸው ህፃናት በአረብ ሀገር ተሰዳ እረጅም አመት አብራቸው የነበረች ሰራተኛ ኮንትራቷን ጨርሳ ወደ ሀገሯ ስትመለስ ሲያለቅሱ እሚያሳይ ቪዲዮ ነው። እሚያለቅሱት ሕፃናቱ ብቻ ሳይሆኑ ወላጆችም ጭምር መለያየታቸውን መቋቋም ከብዷቸዋል።
ህፃናቱ ያደጉት በሷ እጅ በመሆኑ እንደ ሁለተኛ እናታቸው አድርገው ስለሚያዩአት የመለያየቱን ህመም መቋቋም አቅቷቸው በከፍተኛ አቅም ሲያለቅሱ ይታያል።
ወላጆችም አብረው ማልቀሳቸው እህታችን በቤታቸው ውስጥ የነበራትን መልካም ስነ-ምግባር፣ ታማኝነት እና የታየችበትን የፍቅር ልክ ግልጽ ያደርጋል።
በአርብ ሀገር ተሰደው እሚሰሩ የማህበራዊ ህይወት ባህልና እሴት መሰረቱ በፍቅር፣ በሩህሩህነት እና ልጅን እንደራስ አይቶ በማሳደግ ላይ የተገነባ ነው። ​ይህ ዓይነቱ ባህሪ በስራ አጋጣሚ ባህር ማዶ በሚሄዱ እህቶቻችን ዘንድ በጉልህ ይታያል፡
ሰራተኞች ልጅን የቤት ሰራተኛ ሆኖ “በስራ መመሪያ” ብቻ ከመንከባከብ ይልቅ በውስጣቸው ባለው  እናትነታዊ ፍቅር ሞልተው ነው የሚያሳድጉት።
የገንዘብ ኮንትራት ሊያልቅ ይችላል፤ በፍቅር፣ በታማኝነት እና በደግነት የተገነባ የሰው ልጅ ግንኙነት ግን ድንበር እና ጊዜ ሳይገድበው በልብ ውስጥ ታትሞ ይኖራል።
ይህ ከላይ በቪዲዮ እንደምታዩት  በውጭ ሀገር የሚሰሩ  እህቶቻችን የሚያሳዩትን መልካም ሰብኦዊነት እና ፍቅር በግልጽ የሚያሳይ፣ እንዲሁም መልካም ስራ እና እውነተኛ ፍቅር ሁልጊዜም ዋጋ እንደለው የሚያሳይ ትልቅ ማስተማሪያ ነው።Via፦ ቤኪ የማርያም ልጅ
     ከንፁህ ፍቅር በላይ ምን ነገር አለ🥰
    
@Seledadotio
@Seledadotio


Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: