“በብር ደመወዝ የሚከፈላቸው ሰዎች ገቢያቸው እጅግ ቀንሷል”፦ የቀድሞው የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት የ #ኢትዮጵያ የምንዛሬ ሪፎርም ድህነትን አባብሷል አሉ
የቀድሞው የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማልፓስ የኢትዮጵያ ብር መዳከም እና የውጭ ምንዛሬ ማሻሻያዎች ድህነትን በከፍተኛ ሁኔታ ማባባሳቸውን በመግለጽ፤ በብር ደመወዝ የሚከፈላቸው ሰዎች «ገቢያቸው እጅግ ቀንሷል» ሲሉ ተናግረዋል። በተቃራኒው ጥቂት ቡድኖች የውጭ ምንዛሬን እና የሀገር ውስጥ ብድርን በልዩ ሁኔታ ማግኘት በመቻላቸው ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ማልፓስ፤ ስታንሊ ፊሸር መታሰቢያ በተሰኘ መድረክ ላይ ባቀረቡት የፖሊሲ ጥናት ላይ ኢትዮጵያን በዋና ምሳሌነት የተጠቀሙ ሲሆን፥ ሀገሪቱ የእርሻ መሬት፣ የተፈጥሮ ሀብት፣ የውኃ፣ ተስማሚ የአየር ንብረት እና የሰው ኃይል አቅም ያላት በመሆኗ «ትልቅ የእድገት አቅም» ያላት ሀገር እንደሆነች ገልጸዋል።
የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ውስጥ ወደ 200 የሚጠጉ ፕሮጀክቶችን በገንዘብ መደገፉንና 43ቱ አሁንም በሂደት ላይ እንደሚገኙ የጠቆሙት ማልፓስ፤ ሆኖም የሀገሪቱ የነፍስ ወከፍ ገቢ አሁንም 1,100 ዶላር አካባቢ በመሆኑ «ከዓለም ደሃ ሀገራት አንዷ» አድርጓታል ብለዋል።
@Seledadotio

No comments yet.