«ገነርስ» የተሰኘው የአርሰናል ደጋፊዎች ማህበር በይፋ ስራ ጀመረ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja:-በኢትዮጵያ የሚገኙ የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ክለብ የአርሰናል ደጋፊዎችን በአንድ ማህበር ስር በማሰባሰብ በኢኮኖሚ፣ በሙያ እና በማህበራዊ ዘርፎች ለማስተሳሰር ያለመው «ገነርስ» የተሰኘ ማህበር በይፋ ሥራ መጀመሩን አስታወቀ።

ማህበሩ በይፋ ሥራ መጀመሩን ባበሰረበት መድረክ ላይ እንደተገለጸው፤ የማህበሩ ዋና ዓላማ የስፖርት ደጋፊነትን ከተለመደው ስፖርታዊ መዝናናት ባሻገር፣ ለአባላቱ ተጨባጭ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ወደ ሚያስገኙ ዕድሎች ማሸጋገር መሆኑ ተገልጿል።

የ«ገነርስ» ማህበር ዋነኛ ትኩረት ደጋፊዎችን በአንድ ሁለንተናዊ መድረክ ስር ማገናኘት ሲሆን፣ ለዚህም ስኬት ከመንግስታዊ እና ከግል ተቋማት ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነቶችን ለመመስረት ማቀዱ ተጠቅሷል።

በተለይም የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለአባላት የሙያ ክህሎት ማሳደጊያ ሥልጠናዎች፣ የሥራ ዕድሎች እና የንግድ አማራጮች እንደሚመቻቹ የተገለፀ ሲሆን አባላት እርስ በእርስ እንዲቀራረቡ እና ልምድ እንዲለዋወጡ የሚያስችሉ ልዩ ልዩ የአባልነት ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ጠንካራ የማህበረሰብ መድረክ ለመገንባት መታቀዱ ይፋ ሆኗል።

በተጨማሪም ማህበሩ አባላቱን የሚያዝናኑ፣ ጠቃሚ መረጃዎችን የሚያጋሩ እና ትምህርታዊ ይዘት ያላቸውን የዲጂታል ሚዲያ ውጤቶች በማዘጋጀት የማህበረሰብ ትስስሩን ይበልጥ ለማጠናከር ማቀዱ በመድረኩ ላይ ተመላክቷል።

«ገነርስ» ማህበር በኢትዮጵያ የስፖርት ደጋፊነት ባህል ላይ አዲስ አሠራር በማስተዋወቅ፣ ደጋፊዎች ስፖርታዊ ፍቅራቸውን ወደ የጋራ ዕድገት እና ማህበራዊ ተፅዕኖ የሚቀይሩበትን አቅጣጫ እንደሚያመቻች ይጠበቃል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: