የፍልሰታ አስራቴን ለመድኃኔዓለም ህንፃ ማስፈፀሚያ

- Advertisement -
Sidebar AD

ፆመ ፍልሰታን የፈረሰውን ቤተክርስቲያን ህንፃ በማስፈፀም በረከት እንድናገኝ ጥሪ ቀርቧል

በሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት በቀይት ወረዳ ሥር የሚገኘው የመለጥ ደብረ ፀሐይ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ከተመሠረተ ከ60 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ታሪካዊ ቤተክርስቲያን ነው።

ነገር ግን እስካሁን እድሳት ባለመደረጉ ምክንያት ጣሪያው እያፈሰሰ ግድግዳው በስብሶ የቤተክርስቲያኑ ቋሚ ምሰሶዎች በምስጥ ተበልተው ቤተክርስቲያኑ ሊወድቅ ተቃርቦ በነበረበት ሰአት እናንተ ደጋግ ክርስቲያኖች ባደረጋችሁት እርዳታ የቤተክርስቲያኑን እድሳት ጀምረናል።

በመሆኑም ይህ ቤተክርስቲያን እድሳቱ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ስለቆመ
ታቦቱን በጊዜያዊነት በማይመች ለታቦቱ ማረፊያ ብቻ ወደተዘጋጀች መቃኞ ስላለ ምእመናን በዝናብና በፀሐይ እያስቀደሰ ስለሆነ ቤተክርስቲያኑ ተጠናቆ ታቦታቱ ወደዋናው መቅደስ እንዲገቡ የእኛን ልጆቿን ድጋፍ ትሻለች

ስለዚህ በኢትዮጵያም ሆነ በውጭ አገር የምትኖሩ የቤተክርስቲያን ልጆች፣ በአቅማችሁ መጠን በመለገስ የእጣን፣ የጧፍ፣ የዘቢብ፣ በመርዳት ፆመ ፍልሰታን እንድናስቀድስ እንዲሁም የህንፃ ቤተክርስቲያናችንን እንድናስፈፅም የአቅማችሁን ድጋፍ እንድታደርጉልን እንጠይቃለን።

የድጋፍ አካውንት:
መለጥ ደብረ ፀሐይ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን
1000756255626

ስልክ: 0920950007

የክርስትናስምዎን በመላክ አባቶች በፀሎት ያስቡዋችኋል

Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2