አለም ለስራዎቻችን የሚገባቸውን ክብር አልሰጠም፦ ሙላቱ አስታጥቄ
#Ethiopia | የኢትዮ ጃዝ አባት ሙላቱ አስታጥቄ ለአፍሪካ ባህላዊና ሀገር በቀል የጥበብ ስራዎች በአለም መድረክ ላይ ተገቢው ክብርና እውቅና አልተሰጣቸውም ሲል ተናግሯል።
የኢትዮ ጃዝ ሙዚቃ ስልት መሥራችና ባለቤት የሆነው አንጋፋው ባለብዙ መሣሪያ ተጫዋቹ ሙላቱ አስታጥቄ የአፍሪካ ሀገር በቀል የጥበብ ስራዎች እና ባህላዊ ሙዚቃዎች የሚገባቸው ዓለም አቀፋዊ እውቅና እና ክብር እንዲሰጣቸው ጥሪ አቅርቧል።
የኢትዮ ጃዝ የሙዚቃ አባት ሙላቱ አስታጥቄ ከ ዘጋርዲያን ጋር ባደረገው ቆይታ ስለ ኢትዮጵያና አፍሪካ ባህላዊና ሀገር በቀል የሙዚቃ ስራዎች ሰፊ ማብራርያ ሰጥቷል።
የኢትዮ ጃዝን አዲስ የሙዚቃ ስልት በ1960ዎቹ ለመጀመሪያ ጊዜ ለህዝብ ሲያስተዋውቅ ከፍተኛ ተቃውሞና ፈታኝ ሁኔታዎች ገጥመውት እንደነበር አስታውሷል።
ሙላቱ አስታጥቄ ባለፉት ሁለት አሥርት አመታት ይህ ድንቅ ስልት በዓለም አቀፍ ደረጃ እጅግ የተወደደና የብዙዎችን ቀልብ መሳብ መቻሉን ገልጿል።
በመሆኑም የአፍሪካን የሙዚቃ ሀብትና ባህላዊ እሴቶች ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ የቀደሙትም ሆነ የዛሬዎቹ ሀገር በቀል የጥበብ ስራዎች የሚጫወቱት ሚና ትልቅ በመሆኑ ተገቢውን ክብር ማግኘት እንዳለባቸው አሳስቧል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Ethiojazz #music
#theGuadian #MulatuAstatke
Source: GetuTemesgen









No comments yet.