የሼክ ሙሐመድ አል አሙዲ ሀብታቸው እየጨመረ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በኢትዮጵያ ቀዳሚው ባለሀብት ሼክ ሙሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ጠቅላላ የሀብት መጠናቸው 10.1 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ተከተሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ በ10 ቢሊዮን ዶላር የሀብት ማማ ላይ ከተቀመጡ የዓለማችን ቢሊየነሮች ክበብ ውስጥ ዳግም ተቀላቀሉ።

እንደ ብሉምበርግ ቢሊየነርስ ኢንዴክስ አዲስ መረጃ የሳዑዲ-ኢትዮጵያዊው ቢሊየነር ሀብት ከፈረንሳይኞቹ ዓመት መ ካት ጀምሮ በ1.67 ቢሊዮን ዶላር ወይም በ19.7 በመቶ እድገት በማሳየቱ በዓለም አቀፍ የሀብታሞች ዝርዝር ውስጥ በ375ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

በኢንዱስትሪ፣ በኢነርጂ እና በበርካታ ዘርፎች ላይ ባሏቸው መዋዕለ ንዋዮች ላይ የታየው ከፍተኛ የገበያ ዋጋ ጭማሪ ለዚህ የሀብት እድገት ዋና ምክንያት የሆነ ሲሆን ይህም የሀገራችን ቁጥር አንድ ባለሀብትነታቸውን ይበልጥ ያጠናከረ አጋጣሚ ሆኗል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1