#Ethiopia | በኢትዮጵያ የስፖርት ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቅ ትኩረትን የሳበውና ለሁለተኛ ጊዜ በዘመናዊና ታሪካዊ መልኩ የሚሰናዳው “የአድዋ ፋይት ናይት” የድብልቅ ማርሻል አርትስ ፣ የሙአይ ታይ እና የቦክሲንግ ውድድር የመጨረሻው ዝግጅት ላይ ይገኛል።
የፊታችን ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደውን ይህን ታላቅ ስፖርታዊ ሁነት አስመልክቶ በዛሬው ዕለት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የጋዜጣዊ መግለጫ እና የፋይተሮች ፍትጫ መርሃ ግብር ተካሂዷል።
በስዌት ቦክስ ጂም፣ በሸጋ ኤቨንትስ እና በአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት የቀረበው ይህ ውድድር፣ ሶስቱን የፍልሚያ ስፖርቶች በአንድ መድረክ ላይ በማ አስተናገድ በአይነቱ ልዩና ድምቅ ያለ ምሽት እንደሚያሳልፍ አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
በዕለቱ በሚካሄዱት 11 የተመረጡ ፍልሚያዎች ውስጥ 4 የቦክስ፣ 4 የኤምኤምኤ እና 3 የሙአይ ታይ ጨዋታዎች የተካተቱ ሲሆን፣ የቀድሞው ሻምፒዮን ዮሐንስ ስለሺ (ጆኒ) ከሴዶ ማርሻል አርት (ካሚል) ጋር የሚያደርጉት የኤምኤምኤ ፍልሚያ የዕለቱ ዋነኛ የትኩረት ማዕከል እንደሚሆን ይጠበቃል።
በተጨማሪም ዝግጅቱ ለሴቶች ተሳትፎ ልዩ ቦታ የሰጠ ሲሆን፣ በታይላንድ ሀገሯን ወክላ ድንቅ ድል ያስመዘገበችው ዘሃራ ከብታጅራዋ አትሌት አብስላት ጋር የምታደርገው የሙአይ ታይ ፍልሚያ የምሽቱ ሌላኛው አጓጊ ትዕይንት ነው።
የስዌት ቦክስ ስራ አስኪያጅ አቶ ጌታቸው መለሰ በመርሐግብሩ ላይ እንደገለጹት ይህን ታላቅ የውድድር ምሽት ለመታደም የሚመጡ ተመልካቾችን መጉላላት ለመቀነስ ሲባል የዲጂታል ቲኬት ሽያጭና የተቆጠረ የወንበር አሰራር የተዘረጋ ሲሆን የውድድሩ የዳኝነትና የነጥብ አቆጣጠር ሙሉ በሙሉ በቦክስ እና በኢንተግሬትድ ማርሻል አርት ፌዴሬሽኖች ሙያዊ ኃላፊነት የሚመራ መሆኑን አቶ ጌታቸው መለሰ ገልጸዋል።
በቀጣይም በሀገራችን ያልተለመዱ የጥንካሬና የመስዋዕትነት ፈታኝ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በስፋት ለማስተዋወቅ መታቀዱን ገልጸዋል።
ጌትነት ተመስገን
📷ከበደ መክብብ
#MMAEthiopia #EthiopianBoxing
#MuayThaiEthiopia #AdwaFightNight
#EthiopianFighters#AdwaVictoryMemorial



Source: GetuTemesgen









No comments yet.