በሰሜን ኸዋ ሀገረ ስብከት በጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም ድንገት በተከሰተ ርዕደ መሬትና የመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ5 ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ሀገረ ስብከቱ አስታወቀ ።
በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በታላቋ ገዳም ደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ቅድስት ማርያም ገዳም ከክረምቱ መግባት ጋር ተያይዞ በተከሰተው ከፍተኛ የዝናብና የመባርቅት ድምፅ በደረሰ ርዕደ መሬትና የመሬት መንሸራተት ለጸበል ፣ ለሱባኤና ለመሳለም ከአራቱም አቅጣጫ በተሰበሰቡ በጻድቃኔ ማርያም ልጆችና ወዳጆች ላይ የደረሰው ድንገተኛ አደጋ እጅግ አስደንጋጭና ልብ ሰባሪ ኃዘን መኾኑ ተገልጧል።
በዚህ ድንገተኛ አደጋም የ14 ወገኖቻችን ሕይወት ሲያልፍ በ5 ወገኖቻችን ላይ ከፍተኛና በ2 ወገኖች ላይ መለስተኛ ጉዳት መድረሱም ተመላክቷል።
የሀገረ ስብከቱ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቀሌምንጦስ በስፍራው በመገኘት ለሞቱ ወገኖቻችን ጸሎተ ፍትሐት ለተጎዱት ጸሎት ላዘኑ ወገኖቻችን የማጽናኛ ትምህርተ ወንጌልና አባታዊ ቃለ በረከት በመስጠት ላይ ይገኛሉ ።
© የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት አቡቀለምሲስ ሚዲያ

Source: Yeneta Tube









No comments yet.