በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ
 
በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።
 
የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት በቴክኖሎጅ ታርሞ ይፋ የተደረገ ሲሆን በክልሉ 194374 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸው ይታወቃል። ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች መካከልም 165342(85.06%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት አስመዝግበዋል። ይህም ከባለፈው አመት ተመሳሳይ አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር የ3% ብልጫ አሳይቷል።
 
ተማሪዎች በሁለት አማራጮች ውጤታቸውን ማየት የሚችሉ ሲሆን :-
 
➊ በኮምፒውተር ወይም ስልካቸው ባለዉ የድር መፈለጊያ መተግበሪያ ( Web browser Application ) ላይ
1) ለ6ኛ ክፍል ተፈታኞች https://amhara6.ministry.et/#/result የሚለውን አድራሻ በመፃፍ
2) በሚመጣው ቅጽ (form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) እና ስም በአማርኛ በማስገባት
3) ዉጤት ይመልከቱ (Check your result) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማየት ይችላሉ፡፡
 
❷ በተጨማሪም @emacs_ministry_result_qmt_bot በሚለው የቴሌግራም ቦት ላይ በመግባት ተማሪዎች ውጤታቸውን መመልከት የሚችሉ ሲሆን ለመጀመሪያ
1) start የሚለውን ይጫኑ!
2) በመቀጠልም ክፍልዎን ይምረጡ
3) ከዚያም ክልልዎን ይምረጡ
4) በመቀጠል የምዝገባ መለያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስምን በማስገባት ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።
ተማሪዎች ማንኛውም ከውጤት ጋር የተያያዘ ቅሬታ ካላቸው ማቅረብ ይችላሉ። ቅሬታቸውንም ለማቅረብ
 
➌ በኮምፒውተር ወይም ስልካቸው ላይ ባለዉ የድር መፈለጊያ መተግበሪያ ( Web browser Application )
 
1) ለ6ኛ ክፍል ተፈታኞች https://amhara6.ministry.et/#/complaint የሚለውን አድራሻ በመፃፍ
2) በሚመጣው ቅጽ(form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) እና የተማሪውን የመጀመሪያ ስም (First Name)በማስገባት
3) የትምህርት ዓይነት አሳይ(Fetch course) የሚለውን ቁልፍ በመጫን
4) ቅሬታ ማቅረብ የሚፈልጉበትን ይምረጡ
5) በመጨረሻም ሪፖርት (Add Complaint) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ።
 
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: