የጤናው ዘርፍ የአረንጓዴ አሻራ ተሳትፎ

- Advertisement -
Sidebar AD


‎📌 ከ30 ሺህ በላይ ችግኞች በዛሬው እለት ተተክለዋል

‎#Ethiopia | ​በሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ላይ የጤና ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች እንዲሁም ሰራተኞች ከኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ከገፈርሳ ጉጄ ክፍለ ከተማ ጋር በመተባበር በዛሬ እለት በገፈርሳ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ዳርቻ ከ30 ሺህ በላይ ችግኞች በዛሬው እለት ተተክለዋል።

‎በሸገር ከተማ በገፈርሳ ጉጄ አካባቢ በተካሄደው በዚህ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ የጤና ሚኒስትሯ ክብርት ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች እና የየደረጃው የአካባቢው አመራሮች እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላትና የማህበረሰብ ክፍሎች ከማለዳው 1 ሰዓት ጀምሮ በመገኘት ችግኝ ተክለዋል።

‎​የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፣ አረንጓዴ አሻራ እና የጤና ዘርፍ የማይለያዩ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። ችግኝ ለአካባቢ ጥበቃ ብቻ ሳይሆን ለህብረተሰብ ጤና፣ ለንጹህ አየር እና ለምግብ ዋስትና ማሻሻያ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው፣ በተለይም ለአዲስ አበባ እና ለአካባቢው ህዝብ የንጹህ ውሃ ምንጭ የሆነውን የገፈርሳ አካባቢን መንከባከብ የሁላችንም ህብረ-ብሄራዊ ሀገራዊ ኃላፊነት እንደሆነ አስገንዝበዋል።

‎​በዕለቱ በቦታው ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትሯ ክብርት ዶክተር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ አካባቢዋን ለመጠበቅ የምታደርገው ጥረት በንግግር ሳይሆን በተግባር የሚገለጽ መሆኑን አብራርተዋል።

‎በዕለቱ ሚኒስቴሩ ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን ከ30 ሺህ በላይ ችግኞችን የተከለ ሲሆን፣ በክረምቱ የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ-ግብር ደግሞ በሀገር አቀፍ ደረጃ እስከ 250 ሺህ ችግኞችን ለመትከል እና ከ20 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ነጻ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

‎​በመጨረሻም ክብርት ሚኒስትሯ፣ የጤና ባለሙያዎች እና መላው የሀገራችን ህዝብ ቀኑ ሳያልቅ እና ጀምበር ሳትጠልቅ የድርሻቸውን ችግኝ በመትከል የዚህ ታሪካዊ ኩነት አካል እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

‎ከችግኝ ተከላው መርሐግብር ባሻገር የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት በሸገር ከተማ ከ200 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።

‎በጌትነት ተመስገን
‎📷 ከበደ መክብብ

‎#MinistryOfHealth ​#TreePlanting
‎​#ClimateAction ​#PublicHealth
‎​#EnvironmentalHealth ​#Gefersa ​#CleanEnvironment ​#GreenEthiopia
‎​#CommunitySupport






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2