ትርፍ አንጀት ምንድን ነው? በተለምዶ ትርፍ አንጀት እየተባለ የሚጠራው ችግር  የሚከሰተው አፔንዲክስ (ትርፍ አንጀት) ሚባለው …

- Advertisement -
Sidebar AD
ትርፍ አንጀት ምንድን ነው?
በተለምዶ ትርፍ አንጀት እየተባለ የሚጠራው ችግር  የሚከሰተው አፔንዲክስ (ትርፍ አንጀት) ሚባለው ትንሽ የአንጀት አካል ሲያብጥ ወይም ሲቆጣ ነው። ይህ ችግር በፍጥነት ካልታከሙ ሊፈነዳ እና አደገኛ ኢንፌክሽን ሊያስከትል ይችላል።
የትርፍ አንጀት ቀዶ ህክምና ምንድን ነው?
የትርፍ አንጀት ቀዶ ህክምና ትርፍ አንጀት ለማስወገድ የሚደረግ ቀዶ ጥገና ሲሆን ለትርፍ አንጀት ችግር በጣም የተለመደው ሕክምና ነው። ቀዶ ሕክምናው በክፍት (open) መንገድ ወይም በላፓሮስኮፒ ሊሰራ ይችላል።
🚨 የትርፍ አንጀት አደገኛ ምልክቶች፡
👉 ከታች በቀኝ በኩል ባለው የሆድ ክፍል ላይ ድንገተኛ እና ከባድ ህመም ፣
🔹ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ ፣
🔹ትኩሳት እና ብርድ ብርድ ማለት፣
🔹 የምግብ ፍላጎት ማጣት እና
🔹 በእንቅስቃሴ የሚባባስ ህመም ሲኖር በፍጥነት ወደ ህክምና መሄድ ያስፈልጋል።
የትርፍ አንጀት ቀዶ ህክምና ለምን ያስፈልጋል?
ትርፍ አንጀት እንዳይፈነዳ እና
ከባድ ኢንፌክሽን እንዳይፈጠር እንዲሁም
በፍጥነት ለማገገም ይህ ቀዶ ህክምና ያስፈልጋል።
ከቀዶ ጥገናው በኋላ ምን ማድረግ ያስፈልጋል?
🔹 በቀላሉ ሊፈጩ የሚችሉ ምግቦችን መመገብ፣
🔹 ረጋ ያለ እንቅስቃሴ ማድረግ፣
🔹 እረፍት ማድረግ እና
🔹 ውሃ በደንብ መጠጣት ቶሎ ለማገገም ይረዳል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: