ብዙ የሀገር ካስማዎችን ያፈራው ፤ ቅዱስ ዮሴፍ ት/ት ቤት

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ታዋቂው የቢዝነስና የኢኮኖሚ አማካሪ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ በልጅነት በተማሩበት ቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት በመገኘት ለ2026 የትምህርት ዘመን 171 ተመራቂ ተማሪዎች የክብር እንግዳ ንግግር አደረጉ።

በዝግጅቱ ላይ የተመረቁት ወጣቶች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግባታቸው የተገለጸ ሲሆን የዓመቱ ከፍተኛ ውጤት ያመጣው ተማሪ በታዋቂው የአሜሪካው የት/ት ተቋም (Yale University) ሙሉ የነፃ ትምህርት እድል ማግኘቱ ተበስሯል።

​አቶ ዘመዴነህ በንግግራቸው ቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት ከተመሳሳይ ትምህርት ቤቶች አንጻር በዝቅተኛ ወጪ ከፍተኛ ጥራት ያለው ትምህርት በመስጠት በርካታ ሀገር ተረካቢ መሪዎችን ማፍራቱን ገልጸዋል።

አያይዘውም ለተመራቂዎቹ ጠንክሮ በመስራት የራስን እድል መፍጠር፣ በስነ-ምግባር መመራት፣ ውድቀትን እንደ መልካም የትምህርት አጋጣሚ በመቁጠር አለመፍራት እና አሁን በሀገሪቱ እያደገ ባለው ኢኮኖሚ የተፈጠሩ እድሎችን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

​የአፕል ኩባንያ መስራች ስቲቭ ጆብስን “stay hungry, stay foolish” የሚለውን ታዋቂ አባባል በመጥቀስ ንግግራቸውን ያጠናቀቁት አቶ ዘመዴነህ፣ በዝግጅቱ ወቅት በዝቅተኛ ገቢ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍላ ልጇን በላቀ ውጤት ካስመረቀች እናት ጋር ያደረጉት ቆይታ ግሩም እንደነበር ገልጸዋል።

በመጨረሻም ለሁለተኛ ጊዜ በክብር እንግድነት የጋበዟቸውን የትምህርት ቤቱን ፕሬዝዳንት ወንድም ጌታቸውን እና የአስተዳደር ሰራተኞችን አመስግነዋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1