📌 የ6ኛ ክፍል ውጤቱ ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ነው
#Ethiopia |የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ይፋ አድርጓል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ አብዮት ደምሴ እንደገለጹት፣ የዘንድሮው ማለፊያ ነጥብ ለሁለቱም ክፍሎች ክልላዊ 50 እና ከዚያ በላይ እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን፣ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ አካባቢዎች ደግሞ 48 እና ከዚያ በላይ እንዲሆን ተደርጓል።
በዚህም መሠረት በ8ኛ ክፍል ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡት 86 ሺህ 502 ተማሪዎች መካከል 78 ሺህ 203 የሚሆኑት ተፈትነው 47 ሺህ 307 ተማሪዎች ማለፊያ ነጥቡን በማስመዝገብ ወደ ቀጣይ ክፍል ተዛውረዋል።
ይህም የክልሉን አጠቃላይ የማለፍ ምጣኔ 60.4 በመቶ የሚያደርሰው ሲሆን፣ ከአምናው የ63 በመቶ ውጤት ጋር ሲነፃፀር የ3 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል።
በተቃራኒው በ6ኛ ክፍል ከተፈተኑት 110 ሺህ 566 ተማሪዎች ውስጥ 70 ሺህ 584ቱ ማለፊያ ነጥብ በማምጣት ያለፉ ሲሆን፣ የክልሉ የማለፍ ምጣኔ 63.8 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል። ይህ ውጤት ከአምናው የ56 በመቶ አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ እድገት የታየበት ነው።
ከትምህርት ቤቶች አፈፃፀም አኳያም በ8ኛ ክፍል 540 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ማሳለፍ ሲችሉ፣ 155 ትምህርት ቤቶች ግን አንድም ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም።
በ6ኛ ክፍል ደግሞ 476 ትምህርት ቤቶች 100 በመቶ የማሳለፍ ስኬት ሲያስመዘግቡ፣ 81 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ ሳያሳልፉ ቀርተዋል።
የክልል ትምህርት ቢሮ
#SouthEthiopia #EthiopiaEducation #MinistryOfEducation #Grade8Exam #Grade6Exam
Source: GetuTemesgen









No comments yet.