በፕሬዚዳንቱ ገደብ ውስጥ ኢትዮጵያም ተካታለች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ፣ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ዚምባብዌ፣ ቡሩንዲ እና ሴኔጋልን ጨምሮ የ30 የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች ለንግድና ለጉብኝት (B1 እና B2) ወደ አሜሪካ ለመጓዝ የቪዛ ማመልከቻ በሚያስገቡበት ወቅት እስከ 20 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የዋስትና ማስያዣ እንዲከፍሉ የሚገደዱበት አዲስ መመሪያ ተጣለ።

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ይህ አሰራር የቪዛ ጊዜያቸውን አጠናቀው በህገ-ወጥ መንገድ የሚቀሩ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስ ያለመ ነው ሲል ገልጿል።

በአንጻሩ የስደተኞች እና የጉዞ መብት ተሟጋቾች ውሳኔው ህጋዊ ተጓዦችን በማስደንግጥና ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና በመፍጠር ህጋዊ የሆኑ ጉዞዎችን የሚያስቀር ነው ሲሉ ተችተውታል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: