#Ethiopia | ስመጥሩ የሆሊውድ ተዋናይና ዳሬክተር ቤን አፍሌክ በውድድር ያሸነፈውን 1 ሚሊዮን ዶላር በኮንጎ ለሚገኘው የተራድኦ ድርጅት አበርክቷል።
አፍሌክ በኤቢሲ የቴሌቪዥን ጣቢያ በሚቀርበው Who Wants to Be a Millionaire? ውድድር ላይ ተሳትፎ የ1 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት በማሸነፉ ነው ልገሳውን ያደረገው።
ቤን አፍሌክ ከባልደረባው ጋር ሁሉንም ጥያቄዎች በትክክል ከመለሱ በኋላ አሸናፊ ሆነዋል።
በውድድሩ ያገኙትን የ1 ሚሊዮን ዶላር ሙሉ ሽልማት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለሚገኝው የእርዳታ ድርጅት አበርክቷል።
አፍሌክ ሙሉ ገንዘቡን በ2010 እራሱ ተባባሪ መስራች ሆኖ ላቋቋመው ለተሰኘው የበጎ አድራጎት ድርጅት አበርክቷል።
ድጋፉ በምስራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለሚገኙ የእርዳታ ድርጅቶች መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲያገኙ ይደረጋል ብሏል።
እንዲሁም ድጋፉ በአካባቢው በሰላምና ፀጥታ እንዲሁም በፍትህ ስርአት ለሚሰሩ ተቋማት ይውላል ነው የተባለው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#BenAffleck #Thanksgiving
#JimmyKimmel #ECI
Source: GetuTemesgen









No comments yet.