አርሰን ቬንገር እቅጩን ተናገሩ።

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የቀድሞው የአርሴናል አሰልጣኝ እና የአሁኑ የፊፋ የዓለም አቀፍ እግር ኳስ እድገት ኃላፊ አርሰን ቬንገር የፊፋ ፕሬዝዳንት ጃኒ ኢንፋንቲኖ ያቀረቡትና ሳይሳካ የቀረው የንግድ እቅድ ያወቁት በሚዲያ ዘገባዎች ነበር አሉ።

ቬንገር አክለውም ፊፋ ፕሮጀክቱን ለመሰረዝ የወሰደው እርምጃ ፍጹም አስፈላጊና ጥያቄ ውስጥ የማይገባ ነው ብለዋል።

እኔ በዚህ ስትራቴጂካዊ እቅድ ውስጥ ምንም ዓይነት ተሳትፎ አልነበረኝም ስለ ፕሮጀክቱም ለመጀመሪያ ጊዜ ያወቅኩት በሚዲያ ዘገባዎች አማካይነት ነው ብለዋል።

ፊፋ የዓለም ዋንጫን ጨምሮ ዋና ዋና ውድድሮቹን የንግድ እንቅስቃሴዎች ለግል ባለሀብቶች በመሸጥ ቢሊዮን ዶላሮችን ለማሰባሰብ አቅዶ ነበር።

እቅዱ ግልጽነት የጎደለው እና የእግር ኳስን ንግድ ብቻ ማዕከል ያደረገ ነው በሚል ተቃውሞ ገጥሞት ነበር።

የተፈጠረውን አለመግባባት እና ክፍፍል ለማስወገድ ሲባል የፊፋ ፕሬዝዳንት ጃኒ ኢንፋንቲኖ እቅዱ ሙሉ በሙሉ መሰረዙን ይፋ አድርገዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#ArseneWenger
#Arsenal #global #football #development #FIFA


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2