#Ethiopia | አዲስ በታተመ ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ኢንዴክስ መሠረት፣ ኢየሩሳሌም ከቴል አቪቭ በከፍተኛ ደረጃ ተሻሽላ መመዝገቧ ተገልጿል።
በዚህ ደረጃ ኒው ዮርክ፣ ፓሪስ እና ኦሳካ በቅደም ተከተል የዓለም ምርጥ የቱሪስት ከተሞች ሆነው ሲመረጡ፣ ኢየሩሳሌም በአጠቃላይ 48ኛ ደረጃን በመያዝ በከፍተኛው የምድብ ደረጃ ተካትታለች። በባህልና ታሪክ ዘርፍ ደግሞ በዓለም 10ኛ ደረጃ ተቀምጣለች።
በተቃራኒው ቴል አቪቭ በአጠቃላይ 120ኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ሦስተኛው የምድብ ደረጃ ወርዳለች።
ጥናቱ የተዘጋጀው በYanolja Research ከPurdue University እና Kyung Hee University ጋር በመተባበር ሲሆን፣ በ14 ቋንቋዎች የተደረጉ የማኅበራዊ ሚዲያ የቱሪዝም ውይይቶችን በመተንተን ውጤቱን አዘጋጅቷል። ከተለመዱት እንደ የጎብኚዎች ቁጥር ወይም የሆቴል አቅም ያሉ መለኪያዎች ይልቅ፣ ጥናቱ ቱሪስቶች ከተሞችን እንዴት እንደሚገነዘቡና ስለእነሱ ምን ያህል አዎንታዊ አስተያየት እንዳላቸው ለመለካት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
የኢየሩሳሌም ውጤት
– አጠቃላይ፡ 48ኛ
– በግንዛቤ/ዕውቅና፡ 39ኛ
– በጎብኚዎች ልምድ፡ 63ኛ
– በባህልና ታሪክ፡ 10ኛ
– በከተማ ውበትና ተፈጥሮ፡ 52ኛ
– በእንግዳ አቀባበል፡ 65ኛ
– በቱሪዝም ይዘት፡ 93ኛ
የቴል አቪቭ ውጤት
– አጠቃላይ፡ 120ኛ
– በግንዛቤ/ዕውቅና፡ 96ኛ
– በጎብኚዎች ልምድና አዎንታዊ አስተያየት፡ ከ200 ከተሞች 195ኛ
– በእንግድነት፡ 93ኛ
– በባህልና ታሪክ፡ 118ኛ
– በቱሪዝም ይዘት፡ 124ኛ
– በከተማ ውበት፡ 136ኛ
ይህ ውጤት የታተመው፣ በ«Travel + Leisure» መጽሔት የ2026 የዓለም ምርጥ ከተሞች ደረጃ ኢየሩሳሌም በዓለም 7ኛ፣ በአፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ ደግሞ አንደኛ በመሆን ከተመረጠች በኋላ መሆኑ ተጠቁሟል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
Source: GetuTemesgen









No comments yet.